የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፪

ከውክፔዲያ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፪

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

፯ ፤ እሳታውያን የሚሆኑ ሱራፌልና ኪሩቤል ሊነኩት የማይቻላቸው በዕውነት እሳት ነው ።
፰ ፤ ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን ዕውነተኛ የጽድቅ መብልንና ዕውነተኛ የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና ።
፱ ፤ የሐዋርያት ተከታዮች የሆናቹህ በአንብሮ እድ የተሾማቹህ አባቶች ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ለኛ የምታማልዱ እናንተን ተቀብለናቹኋል እካን ። ከእግዚአብሔር ዘንድ ለኛ የሚያማልዱ እነዚህንም ሁለቱን የጳጳሳት አለቆች በዘመናችን ተቀብለናቸዋል የታላቂቱን አገር የኢትዮጵያን አባ ተክለ ሃይማኖትን በአባቶቻችን አገር ከተማ ላይ ክቡር የሚሆኑ አባ...
፲ ፤ ብፅዕትና ፍሥሕት በሁሉ ዘንድ የተመሰገንሽ ቡርክትና ቅድስት ንጽሕትም ስለሆነች ስለአምላክ እናት ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ።
፲፩ ፤ ቅዱሳን ክቡራን ረቂቃን ሰማያውያን ኃያላኖችም ስለሚሆኑ ስለ መላእክት አለቆች ሰባኪ ጎዳናንም ስለ ጠረገ ስለ ዮሐንስ መጥምቅ የተመሰገኑ ቅዱሳን አገልጋዮችም ስለሚሆኑ ስለ አራቱ ወንጌላውያን ማቴዎስና ማርቆስ ሉቃስና ዮሐንስ ።
፲፪ ፤ ስለ ቅዱሳን ባሮችህ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስና እንድርያስ ፊልጶስና በርቶሎሜዎስ ቶማስና ማቴዎስ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ ስምዖንና ማትያን ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ። የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ የጌታችን ወንድም የሚሆን ሐዋርያው ያዕቆብም ። ቅዱስ ምስጉን የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ እስጢፋኖስ ።