የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፮
Appearance
የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፮ | |
---|---|
ዘቅዱስ ሕርያቆስ |
፴፪ ፤ የሙሴ ጽላት ጳጦስ የተባለች የሲና ዕፅ በካህን አሮን ልብስ የነበረች ጸናጽል ዳግመኛም የበቀለችና ያበበች ያፈራችም በትር አንቺ ነሽ ።
፴፫ ፤ የእያሱ የምስክሩ ሐውልት ፣ የጌድዮን ፀምር ፣ የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይና የዘይት ቀንድ አንቺ ነሽ ። የተመካባት የዕሴይ ሥር የአሚናባድም ሠረገላ የዳዊት መሰንቆ የሰለሞንም አክሊል አንቺ ነሽ ። የታጠረች ተክል የተዘረጋች የውኃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ ።
፴፬ ፤ የኤልያስ የወርቅ መሶብ የኤልሳዕ ጋን አንቺ ነሽ ። ኢሳያስ ፅንስን ከድንግልና ጋር የተናገረልሽ ዳንኤልም ያለ ሩካቤ መውለድን የተናገረልሽ አንቺ ነሽ ።
፴፭ ፤ ፋራን የምትባል የዕንባቆም ተራራ የተዘጋች የሕዝቅኤል ምሥራቅ የቤተ ልሔም ሕግ መውጫ ኤፍራታ የምትባል ምድር አንቺ ነሽ ። የሲሎንዲስ ዕፀ ሕይወት የናሆምንም ቁስል የምታድን የዘካርያስ ደስታው የሚልክያስ ንጹሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ ።
፴፮ ፤ ድንግል ሆይ የነብያት ትንቢትና ምሳሌ የሐዋርያት ሞገሳቸው የሰማዕታት እናታቸው የመላእክት እኅታቸው አንቺ ነሽ ። በመዓልትና በሌሊት በበሮችዋ ደጅ የሚጠኑ የወራዙትና የደናግል የመነኮሳትም መመኪያቸው አንቺ ነሽ ።