የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፯

ከውክፔዲያ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፯

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፴፯ ፤ ድንግል ሆይ በኃጢያት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ ።
፴፰ ፤ ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ።
፴፱ ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ ።
፵ ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ ።
፵፩ ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ።
፵፪ ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም የሰማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ ። እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ ።
፵፫ ፤ ድንግል ሆይ ለዮሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም ንጹሕ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ ። እንዲሁ ስለሆነ ።
፵፬ ፤ እርሱ ቅሉ እግዚአብሔር አብ ንጽሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ መልአኩን ወደ አንቺ ላከ ። መንፈስ ቅዱስ በላይሽ ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድልሻል አለሽ ።