የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፰
Appearance
የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፰ | |
---|---|
ዘቅዱስ ሕርያቆስ |
፵፭ ፤ ከአባቱ አጠገብ ሳይለይ ቃል ወዳንቺ መጣ ሳይወሰን ፀነስሽው በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨምር በመኀፀንሽ ተወሰነ ።
፵፮ ፤ መጠንና መመርመር የሌለበት እሳተ መለኮት በሆድሽ አደረ በምድራዊ እሳት እንመሰለው ዘንድ አይገባንም ለእሳትስ መጠን አለው ልክም አለው መለኮት ግን ይህን ያህላል ይህንንም ይመስላል ሊባል አይችልም ።
፵፯ ፤ ለመለኮት እንደ ፀሐይና እንደ ጨረቃ ክበብ እንደ ሰውም መጠን ያለው አይደለም ። ድንቅ ነው እንጂ የሰው ኅሊና የመላዕክትም አእምሮ በማይደርስበት በአርያም የሚኖር ነው እንጂ ።
፵፰ ፤ ለመለኮት ወርድና ቁመት ላይና ታች ቀኝና ግራ ያለው አይደለም በሁሉ የመላ ነው እንጂ ።
፵፱ ፤ ለመለኮት የሚዘረጋበት የሚሰበሰብበት ያለው አይደለም ። ግዛቱ ባገር ሁሉ ነው እንጂ ።
፶ ፤ ለመለኮት በላይ ጠፈር በታችም መሠረት ያለው አይደለም ጠፈሩ እርሱ መሠረቱም እርሱ ነው እንጂ ።
፶፩ ፤ ለመለኮትከምድር ከውስጥዋ የሆነውን ያነሳ ዘንድ ማጎንበስ ራስንም ዝቅ ማድረግ ያለበት አይደለም ለጴጥሮስ እንዳሳየው ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው እንጂ ።
፶፪ ፤ ለመለኮት በሚታይ ገንዘብ በሚወሰንም ገንዘብ ደረትና ፊት የኋላም ጀርባ ያለው አይደለም በነደ እሳት የተሸፈነ ነው እንጂ ። ነደ እሳት ግን እርሱ ነው ። መለኮትስ ንጹህና ጽሩይ ብሩህም ነው ።