የማግ ኢጠ ውግያ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ማግ ኢጠአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ የአይርላንድ መጀመርያው ውግያ ነበረ።

ለዚሁ ውግያ ታሪክ ዋና ምንጮች 3 ናቸው፦

ፓርጦሎን በአይርላንድ 10 ዓመት ከደረሰ በኋላ (2274 ዓክልበ. ገደማ)፣ «ስለምና ማግ ኢጠ» በተባለ ሜዳ በፎሞራውያን አለቃ በኪቆል ግሪከንቆስ («ኪቆል ሽባ-እግር») ላይ ድል አደረገው። የኪቆል ወገን 200 ወንዶችና 600 ሴቶች ከነእናቱ ሎት ሉዋምናሕ ጠቀለለ። እነዚህ በስላይጎ ወሽመጥ በ4 መርከቦች ላይ መጡ። (በሴጥሩን ኬቲን ዘንድ 300 ወንዶችና 300 ሴቶች በ6 መርከቦች ነበሩ።) አንዳችም ሰው ሳይሞት ውግያው አንድ ሳምንት ሙሉ እንደ ፈጀ፣ በፎሞራውያንም ሥራዊት በኩል አንድ እጅ ወይም እግር ያጣ ሰው እንደ ነበር ይጨመራል።