የሜዳ አህያ

ከውክፔዲያ
(ከየሜዳ ኣህያ የተዛወረ)
?የሜዳ አህያ
Equus quagga boehmi
Equus quagga boehmi
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ጐደሎ ጣት ሸሆኔ Perissodactyla
አስተኔ: የፈረስ አስተኔ Equidae
ወገን: የፈረስ ወገን Equus
ንኡስ ወገን: Hippotigris / Dolichohippus
ብቸኛ ዝርያዎች

Equus zebra
Equus quagga
Equus grevyi

የሜዳ አህያላቲን Equidae የሚባለው የፈረስ አስተኔ አባል ሲሆን ፣ በፈረሶች ወገን (Equus) ውስጥ ሶስት ዝርያዎች ናቸው። ከመካከለኛው እስከ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ አጥቢ እንስሳ ነው። ነጭና ጥቁር ሰንጠረዥ የለበሰው ቆዳቸው አንድ ምልክታቸው ነው።

የዱር አራዊት የሚያጠኑ ባለሞያዎች (zoologist) የሜዳ አህያ ነጭና ጥቁር ባለሰንጠረዥ ቆዳ ከሚያድኑት አራዊት ለመሰወር እንደሚጠቅመው ይናገራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ አንድ የሜዳ አህያ ከረዣዥም ሣሮች መሃል ሲሆን አብሶ አንበሳ ለይቶ ለማየት እንደሚከበደው በመጠቆም ነው። ለዚህም ዋነኛው ምክኒያት አንበሳ ቀለም ስለማይለይ ነው።