የቻይና ታላቅ ግድግዳ
Appearance
የቻይና ታላቅ ግድግዳ በቻይና ስሜን ጠረፎች ላይ ከጥንት ጀምሮ የተሠሩት የግድግዶች ጣቢያ ነው።
ከ800 ዓክልበ. ጀምሮ የቻይና መሪዎች የስሜኑን ነገዶች ለመከልከል ግድግዶች ያሠሩ ነበር። እንደ ሥዮንግ-ኑ የመሠሉት ስሜናዊ ብሔሮች በየጊዜው በሠረገላዎች ቻይናን የወረሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ ይህም ግድግዳ መሰናከል ኢንዲሆንባቸው ታሰበ።
በዘመናት ላይ ብዙ ሥርወ መንግሥታት ተጨማሪ ግድግዶች፣ የዘበኛ ግምቦችም፣ ተሠሩ ወይም ታደሱ ወይም ተሻሸሉ። በ4 ወይም 5 ሺህ ማይል ላይ ይዘረጋሉ። ይህም እስከ 1636 ዓም ማንቹዎች እስከ ተሻገሩት ድረስ ተቀጠለ።