የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት

ከውክፔዲያ
የአቢዶስ መንግሥት ምናልባት የገዛው የአባይ ክፍል (ቀይ) ከሂክሶስ (አቫሪስ)ና ከጤቤስ መንግሥታት መካከል

የአቢዶስ ሥወ መንግሥት ምናልባት ከ1646-1596 ዓክልበ. ያሕል በአቢዶስጥንታዊ ግብጽ የተመሠረተ መንግሥት ነበረ። ይህ በብዙዎች ዘመናዊ ሊቃውንት አስተሳሰብ ወይም መላ ምት ነው። በዚህ ዘመን ከአቢዶስ የገዙት ታስበው የአንዳንድ ፈርዖኖች ቅርሶች ወይም ጽላቶች ተገኝተዋል።

በዚህ ዘመን የሂክሶስ ወይም 15ኛው ሥርወ መንግሥት ወደ ስሜን፣ የጤቤስ ወይም 16ኛው ሥርወ መንግሥት ወደ ደቡብ ይገኝ ነበር። ነጻነታቸውን ከጤቤስ 1646 ዓክልበ. አገኝተው ለሂክሶስ በ1596 ዓክልበ. እንደ ወደቁ ይመስላል።

ብዙ ሌላ ስለነዚህ ፈርዖኖች አይታወቅም። የሚከተለው ፈርዖኖች ከአቢዶስ እንደ ገዙ ይታስባል። ቅደም-ተከተላቸው አይታወቅም።

 • ሰኸምራነፈርካው ወፕዋወተምሳፍ - ከአንድ ጽላት ይታወቃል።
 • ሰኸምሬኹታዊ ፓንጨኒ - ከአንድ ጽላት ይታወቃል።
 • መንኻውሬ ሰናይብ - ከአንድ ጽላት ይታወቃል።
 • ወሰሪብሬ ሰነብካይ - መቃብሩ በ2006 ዓም በአቢዶስ ተገኘ።

ቶሪኖ ቀኖና የሚከተለው ክፍል የአቢዶስ ነገሥታት እንደ ዘገቡ ታስቧል፦

 • «ወሰር...ሬ»
 • «ወሰር»[...]
 • (8 መስመሮች ጠፉ)
 • [...]«ሀብሬ»
 • [...] «2» [ዓመት]
 • [...] «2 ዓመት»
 • [...] «4 ዓመት»
 • [...] «3 ዓመት»
 • [...]«ኧንሬ፣ 2 ዓመት»