የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ በናይሮቢ ኬንያ ወደሚገኘው ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለመብረር የተዘጋጀ በረራ ነበር። አውሮፕላኑ መጋቢት 1 2011 (ማርች 10 2019 እ.አ.አ) ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰ ሲሆን ሲጓዙ የነበረ 157 ተሳፋሪዎች ሁሉ ሕይወታቸውን አጡ። አውሮፕላኑ ላይ 149 መንገደኞችና 8 የበረራ ሠራተኞች እየተጓዙ ነበር።

አደጋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተመዘገቡት አደጋዎች በጣም አደገኛው ነው። 1989 (1996 እ.አ.አ) ኮሞሮስ ደሴቶች አቅራቢያ የተከሰከሰውንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 961 በለጠ።

አደጋው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ለመብረር የተዘጋጀ በረራ ነበር። ቦይንግ 737 ማክስ 8 የነበረው አውሮፕላን 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ነበር። አብራሪው ችግር እያጋጠመው መሆኑን እና ወደ አዲስ አበባ መመለስ መፈለጉን አሳውቆ ፈቃድ ተሰጥቷል። ልክ ከዚህ በኋላ የበረራ 6 ደቂቃ እንኳን ሳይሞላ አውሮፕላኑ ከአየር አሳሽ ጠፋ። አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) አቅራቢያ ነው። በአደጋው የተረፈ አልነበረም።[1]

  1. ^ https://www.bbc.com/amharic/live/news-47514163