የኤሲ እና የዲሲ ሲሰተሞች ፍልሚያ

ከውክፔዲያ


 የኤልክትሪክ ኃይልን ለመብራት አገልግሎት ለማዋል የኤሲ እና የዲሲ ሲሰተሞች ፍልሚያ እና እድገቱ[1]
 የኤሲ(ተለዋዋጭ ጅረት) alternating current እና የዲሲ(ቀጥተኛ ዥረት ወይንም ኮረንቲ)  direct current ሲሰተሞች ፍልሚያ ተብሎ የሚታወቀውWar of Currents በ 1880ዎቹ እ.ኤ.አ. የእነዚህ ተወዳዳሪ የኤሌክትሪክ  ኃይል የማስተላለፊያ መንገዶች ዘዴ፤ ማለትም ኢንካነዴሰንት ወይንም አሸብራቂ መብራት ከቀጥተኛ የኤሌክትሪክ ከረንት በታዋቂው ተመራማሪ እና የንግድ ሰው ቶማስ ኤዲሰን  እና የአርክ መብራት ከተለዋዋጭ የ ኤሌክትሪክ  ከረንት በሌላው መሀንዲስ እና የፈጠራ ሰው  ጆርጅ ዌስቲነገሀውስ፤ የደምበኛ ማግኘት፤መያዝ እና መመረጥ ፤ የሲሰተሙ ደህንነት፣እናም ከህዝቡ፣ ከመንግስት እናም እርስ በርስ ያላቸው  የፈጠራ መብት ጉዳይ  ብሎም የእሌክትሪክ ኃይል አምራች ድርጅቶቻቸው እና የሲስተሞቻቸውንም እድገትን ያጠቃልላል፡፡


 በቴሌግራፍ ገኝት ዘመን ወቅት ሀምፍሬይ ዴቭ የተባለው እንግሊዛዊ የኬሚስትሪ ሰው የሁለት ሽቦዎችን ጫፍ  በቻርኮል ወይንም ካርቦን  ሽቦ በማያያዝ ሌላኛውን የሽቦ ጫፍ በባተሪ ሲያግለው ግሎም አርክ መብራት(Davy Lamp, Arc Lamp) ተባለውን ግኝት አስገኘ፤ ጆሴፍ ስዋን የተባለውም እንገሊዛዊ በ1950 አካባቢ ቫኪውም በሆነ አምፖል ውስጥ ሙከራ አድርጎበት ነበር፤ ይሁን እና ይህን ግኝት ለኤሌክትሪክ መብራት ጥቅም እንዲሰጥ አድርገው አልቀረፁትም ነበር፡፡

High voltage electric arc

https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/7/76/Edison_bulb.jpg/330px-Edison_bulb.jpg

   ቶማስ ኤዲሰን (Thomas Edison) - 
 በ1878 ሳይንቲስቱ ቶማስ ኤዲሰን ወደ ስራ ቦታዎች ፤ የንግድ፤እና የመኖሪያ ቤቶች የኤሌክትክ ብርሀን የመስጠት እና የማከፋፈል  ገበያ ጥሩ መሆኑን ተረዳ፤ ይህም በአርክ የኤሌክትሪክ ብረሀን ከፍተኛ ሀይል ያለው መብራት ሰፋ ያለ ስፍራን እንደ መንገድን ለማብራት ይጠቀሙበት ስለነበረ ነው፡፡ ስለዚህም ኤዲሰን እንደዚህ ብሎ ወደ ገበያው ገባ (ኤሌክትሪሲቲን ዋጋውን ዝቅተኛ በማድረግ ለብዙሃኑ እናዳርሳለን በዚህም ሻማን የቅንጦት እናደርጋለን)"We will make electricity so cheap that only the rich will burn candles."


 ስለዚህም በ 1882 ኤዲሰን ኢሉሚናቲንግ ካምፓኔ  Edison Illuminating Company የሚባል ድርጅቱን ከፈተ ስለዚህም ኢንካነዴሰንት አምፖል በመጠቀም በ110ቮ አድርጎ ዘዴውን ቀረፀ፤ በዚህም የመብት ማስከበሪያ ሰነዱን ንግድ ፍቃዱን ከገኘ በሆል የዘዴውን ጥገናም ሆነ ማደግ ተቆጣጠረው፤ለዚህም የክፍያ መቆጣጠሪያ በግልጋሎቱ ልክ የሚቆጥር መለኪያ ሜትርንም አብሮ ፈለሰፈ፤ ይህ ቀጥተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጫ ችግር ጊዜ ከኃይል አጠራቃሚ ምንጭ መስጠቱ፤ኃይል ማመንጫው ወይንም ባትሪው በቀላሉ ከሌላ ጋር መቀጠል መቻሉ ለማስፋፋት ወይንም ፍላጎት ሲቀንስ፤ ይሁን እና ለአጭ ር ርቀት  ብቻ የሚሆን የኤሌክትሪክ  ሀይል ማስተላለፍ መቻሉ እና ለሩቅ ስፍራዎች ማመንጫ ጣቢያዎቹን  እዛው ለምሳሌ ከተማ መሀል መገንባት ማስፈለጉ የዘዴው ድክመቶች ወይንም መሻሻል የሚገባቸው አሰራሮች ነበሩ፡፡


  የኤዲሰን ተፎካካሪ ዲሲ ያለበት መዳረሻዎችንም ጭምር ኤሲ በማስራጨት ጀመረ፤ የኤዲሰን ዘዴ ወፍራማ የኮፐር ሽቦ  መጠቀሙ  ወጪው ከፍተኛ ከመዳረጉ ባሸገር የኤዲሰን ዲሲ ዘዴ የከተሞችን ጨረታ ማጣት ጀመረ፤ በዚም የኤዲሰን አማካሪዎች እና ተቀጣሪዎች ከትላልቅ ከተሞች በስተቀር የእነሱ ዘዴ ተመራጭት እንደማይኖረው ስለዚህም ወደ ኤሲ ገበያ እንዲቡ ቢያስቡም ኤዲሰን ተቃወመው፤ ኤዲሰን ያለው አቆሙ ላይ የፀናው የከፍተኛ ቮልቴጅ ሞት ከማስከተሉ አንፃር እና የሴፍቲ ዘዴዎችንም ለማበልፀግ ገና ረዥም ጊዜ ይወስዳልብሎ ስላመነ ነበር፤ ስለዚህም ምንአልባትም ኤልክተሪክ ለዚህ አይነተ ጥቅም ላይ እንዳይውል በመንግስት ይከለከላል የሚል አስተሳሰብም የያዘ ነበር፤ ስለዚህም ከኤዲሰን ድርጅት እቃ የሚገዙትን እነ ዌስቲንግስተን እና ቶሆምሶን  ጨምሮ በመብት ሰነዶች ጉዳይ ጋርም ብዙ አድክሞቸዋል ፤  በኤዲሰን የዲሲ ማከፋፈያ ዘዴ   ከማመንጫ  ጣቢያው የሚወጣውን ኃይል በወፋፍራም ሽቦዎች ወደ የፋብሪካ ሞተሮች እና ለደንበኛች መብራት የተቀጠሉ ነበሩ፣ በአንድ እና ተመሳሳይ የቮልቴጅ ኃይል መጠንም ነበር የሚዳረሰው ይህም የካረቦኑ (የፊላመንት) ኢንካንዲሰንት ሽቦ በዚህው ኃይል እንዲበራ ተደርጎ  ስለሚፈበረክ ነበር፡፡ American_inventor_and_businessman_Thomas_Alva_Edison.jpg

https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/a/a4/PyramidParthenon.jpg/375px-PyramidParthenon.jpg


  ጆርጅ ዌስቲነገሀውስ (George Westinghouse) - 
 በ1884 የሰሜን አሜሪካው ባለሀብት እና ተመራመሪጆ ዌስቲንግሀውስ ወደ ኤሌክትሪከ ብርሀነ ገበያው ገባ ፤በመጀመረያም የኤዲሰን የዲሲ ሌላኛው ተፎካካሪ ሆኖ ነበረ ነገር ግን በአውሮፓ መፅሄት ዩ.ኬ. የኤንጂነሪንግ ቴክኒክUK technical journal Engineering ያነበበውን የኤሲ ከትራንስፎረመር ጋር በመጣመር ራቅ እሳካለ ስፍራ ድረስ የኤሌክትሪክ ኀይልን ማስተላለፍ እንደሚቻል እናም አምርቶ የሚገኘው  ውጤትም  የተሸለ መሆን ተገንዝቦ፤ በ1887 የዌስቲነግስተኑ ኤሌክትሪክ ድርጅትWestinghouse Electric Companyተመሰረተ በዚህም ዊሊያም ስታንሌይWilliam Stanley, Jr.የተባለውን መሀንዲስ በመቅጠር የሀንጋሪያኖቹን (ዜድ ቢዲ የእና ጊብስ)Gaulard-Gibbs design and designs from the ZBD Transformer የትራንስፎርመር ዲዛይን በመጠቀም የመጀመሪያውን የሚሰራ ትራንስፎርመር ጥቅም ላይ መዋል ቻሉ፡፡

በ1887 መጨረሻ ዌስቲንግስተን 68 የኤሲ ጣቢያዎች ሲኖሩት፤ኤዲሶን 121 ዲሲ ጣቢያዎች ነበሩት፤ ይህም በዚህ እንዳለ እንደ ኤዲሰን ተፎካካሮዎች መብዛታቸው ሁሉ የፓተንት ችግርንም በመሸሽ የየራሳቸውን ዲዛይን በመጠቀም፤ ለምሳሌም የሳውየር ማን ኢንካነዴሰንት አምፖል ዲዛይን ለዌስቲንግሀውስ በመተው ፤ ስለዚህም ሌላኛው ድረጅት ተሆምሰን ሆውስተን ኤሌክትሪክ ድርጅት ከፍተኛ ቮልቴጅ ኤሲ ሴፍቲ ጌዳይ በማሰብ የመብረቅ ተከላላይ ለማስተላለፊያ መስመሩ እንዲሁም የማግነቲክ ስዊች ለኃይል መዛባት ተቆጣጣሪ ሰሩ ይሄን ሲሰተሞች ዌስቲንግስተኑ ድርጅት የለውም ነበር፡፡The_American_entrepreneur_and_engineer_George_Westinghouse_George_Westinghouse.jpg


      ተያያዥ ጉዳዮች


 በኒውዮርክ ከተማ በፖል እንጨት ላይ በተንጠለጠሉት የቴሌግራፍ፤ የስልክ፤  የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ እና አመልካች ገመዶች ከከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሀይል ገመዶች ጋር ተደምሮ ለአይን ብዥ ያለ  ምስል ከመፍጠሩ በተጨማሪ በ1888 በረዶ ክምር ጊዜ መስመሮች በመቆራረጣቸው ደንበኞች ቅሬታ አስነስቶም ነበር፤ ኮንዳክተሩ መሸፈኛ ኢንሱሌተር ወይንም ኤልክትሪክ የማያስተላልፍ ፐላስቲክ  ከሞላ ጎደል ነበር ስለዚህም ለብዙ ሰዎች ህልፈተ ህይወት አስከተለ፤ የ15 አመት እድሜ ልጅ የተቆረጠ የቱሌግራፍ መስመር ከኤልክትሪክ ገመድ ጋር በመነካካቱ፤ ጆን ፊክ የሚባል ዌስተርን ዩኒየን የመስመር ሰራተኛ ከመሬት በላይ በጠንጠለጠለ ሽቦ የዝቅተኛ ቮልቴጅ የቴሌግራፍ መስመር ሲጠግን  ሳይወቀው ከከፈተኛ ኤሌክትሪከ መስመር ጋር በመነካካቱ ወዲያወኑ ሲሞት ለረጀም ጊዜ በሾክ ሰውነቱ ሲርገፈገፍ በሚጨናነቀው የማንሃተን ጎዳና ላይ ብዙ ሰው እያየው ነበር፡፡ በዚህም ወቅት የኒውዮርክ የመገናኛ በዝኋን ወሬቸውን ከኤልክትሪክ ብረሃን ወይስ ብርሀን በጋዝ(የቀድሞውን) ወደ ሞት በሽቦ የሚል አርእስት ቀይረውት ነበር፡፡ እናም የኤሲ አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶች በህግ እንዲጠየቁ ጠይቀው ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ ኤዲሰን ለመጀመሪያ ጊዜ በግልፅ ኤሲ ሲስተምን ኮነነ ፤ ይሁን እና ዌስቲንግ ይህን ሙከራ ተቀውሞ ኤሲ ለማጣጣል  የተደረገ ነው ሲል ይህንንም የሚያሰሩት እነ ኤዲሰን ናቸው ሲል ቅሬታውን አሰማ፡፡

Wires over the streets of New York City

የኒው ኦርሊንስ ታይምስ (Orleans Times-Picayune) እንዲህ ብሎ ዘግቦ ነበር፤ (ሞት ከበራፍ ላይ አይቆምም ነገር ግን ወደ ውስጥ ይገባል ምንአልባትም በሩን ዘግታችሁ መብራቱን ወይንም ጋዙን ስተለኩሱት ሊወስዳችሁ ይችላል)


 ለድንገተኛ ሞት የሚያጋልጥ የኤልክትሪክ አደጋ በዚህ ወቅት አዲስ ነገር ነበር፣ መከላከያ ያልለበሱ የመስመር ሰራተኞች  ለዚህም  ዋንኞች ተጋላጮች ነበሩ፤ ለዚህም የጥርስ ሀኪሙ አልፍሬድ Alfred P. Southwickይሄንን ክስተት ለመቆጣጠር ሲሰራ በውሾች ላይ ሙከራ በማድረግ ብዙ ውሾችን ከገደለ በሆላ እንደውም የኤሲ ዘዴ  ከስቅላት ፍርድ እነደ ተለዋጭ እንደሚያገለግል ታውቆ የኤሌክትሪክ ወንበር electric chair በኒው ዮርክ ፖሊሶች ጥሩ ስቃይ የሌለበት ሆኖ ተገኘ፤ እናም በ1889 ኒውዮርክ የመጀመሪያውን የሞት ፍርድ በኤሌክትሪክ ወንበር ዊሊያም ኬምለርWilliam Kemmler በተባለ ወንጀለኛ ላይ ሞከሩ፡፡
 በሌላም በኩል  ሃሮልድ ብራውን  Harold P. Brown የተባለ ኤሌክትሪክ መሀንዲስ ለኒውዮርክ ፖስት በፃፋው ደብዳቤው የችግሩ መንስኤ ይህ ተለዋዋጭ ሀይል መጠቀም መጀመሩ እናም አደገኛ ከመሆኑ አንፃር ህብረተሰቡን ለቀጥተኛ ሆነ የአደጋ ሁኔታ ውስጥ እንደከተተው እና የኃይል መጠኑን ከ300 ቮልት በታች ማድረግ እንደሚገባ በዚም በወቅቱ የነበሩት ባለሙያዎች የኤሲ እና የዲሲ  ልዩነቶችን በማጤን እውቀታቸውን የፈተኑበት ሆኖም ልክ እንደ ኤሲውም ሁሉ ዲሲው ምንም እንኮን የሞት አደጋ ባያስከትልም  በተለያዩ ቦታዎች ለእሳት አደጋ መከሰት መንስኤ እንደሆኑ ያስረዱበት ወቅት ነበር፡፡


 የሳይንስ ሙከራ ይጎልሃል የተባለው ኤንጂነር ሀርሎድም ከኤዲሰነ ጋር በመወያየት በኮሎምቢያ ኮሌጅ ለተሳታፊዎች በዉሾች ላይ በደረገው ሙከራ፤ በመጀመሪያ አንድን ውሻ እስከ 100ቮ ዲሲ ሾክ ቢያደርገውም ምንም አልሆነም ቀጥሎም በ300ቮ ኤሲ ሌሎች ውሾች ወዲያው ሲሞቱ በማሳየት የኤሲን አደገኝነት አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ግን ኤሲ እያሳየ ካለው እድገት አንፃር ውሳኔ ሊወሰደበት አልቻለም ነበር፡፡
  

መስፋፋት


 ይህ የከረንቶች አጠቃቀም ፍልሚያ ቶማስ ኤዲሰን  እና ጆርጅ ዌስቲነገሀውስ ወደ ክስረት እየከተታቸው ሄደ፡፡ በዚህ ወቅት ዌስቲነገሀውስ ኃይሉን እና አቅሙን በመስፋፋት ሌሎች ድርጅቶችን በመግዛት የሳውየር ማን  የአምፖል ፓተንት በመጠቅለል የኢንደክሽን ሜትር የሚሽከረከር ማግኔቲክ ፊልድ የሚጠቀም በድርጅቱ ውስጥ በማሰራት የኤልክትሪክ ክፍያውን መቆጣጠር ችሎም፤ ኒኮላስ ቴስላን የተባለው ቀድም ብሎ ለኤዲሰን ለመስራት ከ አውሮፓ፤ ቡዳፔስት፤  የመጣ  ቀጥሎም በኤዲሰን ዲሲ ሲሰተም ባለመስማማቱ  በግሉ መስራት ጀምሮ  ቀጥሎም የፖሊፌዝ ኢንደክሽን ሞተር ፓተንትም በማግኘቱ  ከዌስቲንግ ጋር በመስራቱ፤ የጋሊሊኦ ፌራሪስንም  ጨምሮ ከሌሎች የፓተንት ችግሮችም በማቃለል ዌስቲነገሀውስ ድርጅቱን ወደ ተደራጀ ኤሲ ሲሰተም አስገባ፡፡  


  ኤዲሰን በበኩሉ የኤዲሰን ላመፕ ካምፓኒ፣ ኤዲሰን ማሽን ዎረክስ የዳይናሞ እና የኤሌክትሪክ ሞተሮች ፋብሪካ  ፤ በርግማን ናድርጅቱ የሶኬቶች እና ሌሎች የእሌክትሪክ መብራት እቃዎች እና የባሀብቶችንም እገዛ እንደ ጄ.ፒ. ሞረጋን እና የቫነደርቢለት ፋሚሊ እና ሄነሪ ቪላርድ እሱም በበኩሉ ድርጅቱን ለማጠናከር ሞኩሮ  ድርጅቱም አሁን ኤዲሰን ጄኔራል ኤሌክትሪክGeneral Electric ተብሎ ተሰየመ፡፡     

ቀጥሎም ከአምስት አመት በፊት 15 የሚደረሱት የኤልክትሪክ ኩባኝያ ድርጅቶች አሁን ወደ ጄኔራል ኤሌክትሪክ እና ዌስቲነገሀውስ በፋይናንሽያል እጥረት እንዲሁም ኤዲሰን በዲሲተመራጭነት በማጣታቸው አንድ ሆነው መስራት ጀመሩ ይሁን እና ኤዲሶን ድርጅቱ እና የመበት ፍቃዶቹ የሱ ስለነበሩ ቅሬታ ፈጥረውበት ነበር፡፡


 በ1892 ዌስቲነግ በዎርልድስ ኮሎምቢያን ኤግዚቢሽን  የኤሲ ሲስተም ለብዙ እቃዎች ሐይል ሲሰጥ በማሳየቱ በኒያግራ ፎልስ ላይለሚሰራው የመጀመሪያ የኤሲ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ ኮንትረክት አሸነፈ በዚህም የ ኤዲሰን ድርጅት ተቀጣሪ  ቻርልስ ፐ. ስቴይንመየትዝ Charles Proteus Steinmetz የኤሲ ኔትዎረክ የሂሳብ  ማረጋገጫን በማገኘቱ ጄኔራል ኤሌክትሪክም የጨረታው ተካፋይ መሆን ችሎ ነበር በዚህም የዲዛይኖች መሻሻል በአዳዲስ ተቀጣሪ መሀንዲሶች ለትራንስፎርመሮች፤ ለጄኔሬተሮች፤ ለሞተሮች ተገኝቶ ነበር፡፡


 እነደዚህም ሆኖ በ1890 ኤዲሰነ ወደ ሌላ ንግድ () ለመግባት አሰበ ፤ እዲሱ ድርጅትም አሁን በኤዲሰን ሙሉ ቁጥጥር ስር  ያልሆነው ኤሲ እቃዎችን ማምረት ጀመረኤዲሰን አሁን በድርጅቱ ውስጥ ለሚያሰራው ኤሲ ትራንስፎርመር ፈልሳፊ ለሆነው ዊሊያም ስታንሊ ልጅ ለጆርጅ በ1908 ምንአልባትም የኤሲ እድገት እና ውጤትም ተገንዝቦ እንዲህ ብሎት ነበር(እኔ ስህተተኛ ነበረኩ ብለህ  ለአባትህ ንገረው ብሎት ነበር) ፡፡


 ነገር ግን ይህ የፋይናንሺያል ድብልቅ በቴክኒክ በኩል ብዙ ይቀረው ነበር ፤ ያሉትን ሁሉ ሀይል ፈላጊእንደ ፋብሪካ ውስ ጥ ያሉ ዲሲ ሞቶሮች፤ ረጅም ርቀት የሚሄዱ የሀይል መስመሮች ፤ የመኪና ባትሪዎች፤ የከፍተኛ ቮለቴጅ አርክ መበራቶች ፣ ፖሊ ፌዝ  ኤሲ  ኔትዎርኮች፤ ጋር ተቀናጅቶ መስጠት እስፈልጎም ፤ በአውሮፓ እና በአሜሪካ በተገኘየ አዳዲስ ግኝቶች ኤንጂነርድ ዩኒቨርሳል ሲስተም ለመ ጠቀም በዚህም የሞቶር-ጄኔሬተር ጥምረቶችን መጠቀም እናም ሮታሬ ኮንቨርተር የተባሉ ሲሰተሞች ያለው ሲሰተም ከአዲሱ ጋር ማያያዝ አስፈልጎል፡፡

የዕድገት አካሄድ ለምሳሌ - በ1880 በቡረሽ የኤሌክትሪክ ካምፓኒ Brush Electric Company የ3.2 ኪ.ሜ. የመንገድ መብራት በ3500ቮ. የአርክ ብረሀን ለኒው ዮርክ ከተማ ለምሳሌ ተሰራ፡፡ -በ1882 ኤዲሰነ የመጀመሪያውን የፐርል ስትሪት የኤልክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን በማንሀተን በ110ቮ. ለ59 ደምበኞች አቀረበ፡፡ በማሳቹሴትስ የኤሲ ሲስተም በመጠቀም ከ 500ቮ ወደ 100ቮ በመቀየር ለ23 ደምበኞች እስከ 4 ከ.ሜ. ርቀት ላሉ አቀረበ፡፡ በፍራንክፈረት ጀርመን የረዥም ርቀት 175 ኪ.ሜ የኤሲ ከረንት ኃይል ሲሰጥ ተአይንት ቀረበ፡፡ በ1889 የረዥም ርቀት ዲሲ ማስተላለፊያ በ ኦሬጎንWillamette Falls, in Oregon City, Oregon ከተማ ተከፈተ፡ በኒያግራ ፎልስ በ1893 የተጀመረው ዋናው የኤሲ ሲስተም በ25 ሀርትዝ ፍሪኩዌንሲ ነበር ወደ 60 ሀርትዝም በ1950 ነበር የተቀየረው፣ በዚህም ወቅት ቴስላ ኃይል ማመንጫውም ክፍተኛ የኤሲ ኃይል እንዳላውም አረጋግጦም ነበር፡፡

ይህም እድገት እንደዚህ እያለ ቀጥሎ ለምሳሌ የአውሮፓዋ ሄልሰንኪ የዲሲ መስመር እሰከ 1940 ድረስ ነበራት፤ እነ ቦስተን እና ማሳቹሴትስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የ ዲሲ 110ቮ ተጠቃሚ ነበሩ፤ ሆቴል ኒወ-ዮርከሮቹWyndham New Yorker Hotel እስከ 1960 ድረስ የዲሲ መስመር ተጠቃሚ ነበር፡፡ እናም በአሁኑ ወቅት የኤሲ ከረንት ለኤሌክትሪክ ኃይል የብርሀን አገልግሎት በስፋት ለመዋል ችሏል፡፡
  1. ^ https://en.wikipedia.org/wiki/War_of_Currents https://en.wikipedia.org/wiki/Wyndham_New_Yorker_Hotel http://www.thefamouspeople.com/profiles/humphry-davy-6296.php https://en.wikipedia.org/wiki/Nikola_Tesla https://en.wikipedia.org/wiki/Thomas_Edison