የእግዚአብሔር ሰላምና ስምምነት
Appearance
የእግዚአብሔር ሰላምና ስምምነት ወይም በሮማይስጥ Pax et treuga Dei /ፓክስ ኤት ትሬውጋ ደይ/ በዓለም ታሪክ መጀመርያው የታወቀ ሕዝባዊ የሰላም እንቅስቃሴ ነበር። «የእግዚአብሔር ሰላም» መጀመሪያ በ981 ዓም በአሁኑ ፈረንሳይ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪነት የታወጀ ነበር።
ከንጉሡ ካሮሉስ ማግኑስ መንግሥት በኋላ በምዕራብ ፍራንኪያ ወይም ፈረንሳይ፣ የመኳንንት ወገን በሕዝብ ላይ ብዙ መግደልና ዝርፊያ ያድርጉ ነበር። ይህን ለማቃወም፣ በመጀመርያ ቤተክርስቲያኑ በድሆች፣ በቄሶችና በአብያተ ክርስቲያን ላይ ግፍ ማድረጉን ቢከለክሉም ትንሽ ረዳ። በኋላ ከ1033 ዓም በኋላ «የእግዚአብሔር ስምምነት» በአንዳንድ ቀን ከሳምንት መግደልን ከለከለ። ይህንም የሚጥሰው ተወግዞ እራሱ የሚከተለው ግብ ይሆን ነበር። በየጥቂቱ በክፍለዘመናት ላይ ግፍ የተከለከለባቸው ቀኖች ተስፋፉ፣ በመጨረሻም ግፍ ሁሉ በሙሉ ሳምንት ተከለከለ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |