የኦርኾን ጽሑፎች

ከውክፔዲያ

የኦርኾን ጽሑፎች724 ዓም በአሁኑ ሞንጎሊያኦርኾን ወንዝ ሸለቆ በጥንታዊ ቱርክኛና በቻይንኛጎክቱርክ መንግሥት አለቆች የተቀረጹ ሐውልቶች ናቸው። ያስቀረጹዋቸው መሪዎች ቢልጌ ቃጋንና ወንድሙ ኩል ቲጊን ነበሩ።

ጥንታዊ ቱርክኛ እና ቅድመ-ቱርክኛ ከዘመናዊ ቱርክኛ በጣም አይለዩም። እነዚህ ጽሑፎች በማንኛውም የቱርኪክ ቋንቋዎች ቤተሠብ ከሁሉ ቅድመኛ የታወቁት ናሙናዎች ናቸው። የተጻፈበት የኦርኾን ጽሕፈት በተባለው ጥንታዊ ቱርክኛ አልፋቤት ነበረ።

ጽሕፈቶቹ የቱርኮች ታሪክ ይናገራሉ፤ የተንግሪስም እምነት ተከታዮች መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጥንታዊ ቱርኮች ዘላኖችና ወራሪዎች ሲሆኑ፣ ቅዱስ ዋና ከተማቸው «ኦቱከን» በኦርኾን ወንዝ ሸለቆ (በአሁኑ ሞንጎሊያ) እንደ ተገኘ ይገልጻሉ።

«ኦቱከን ከእርሱ አገራት ሊገዙ የሚቻልበት ቦታ ነው... ሁልጊዜ ከኦቱክን ብትገዙ ከዚያም ቅፍለቶችን ብትልኩ ምንም ችግር አይኖርህም...»

በጽሑፎቹም ደግሞ መሪያቸው (ቃጋናቸው) ቢልጌ እንደሚተርከው፣ ቅድም-አያቶቹ ወደ አራት አቅጣጮቹ ዘምተው ጎረቤቶቻቸውን ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ቱርኮች ወደ ቻይና ቀርበው፣ ቻይናዎች በወርቅብርማሽላ (አረቄ) እና በተለይ በሐር ሀብታሞች ስለ ነበሩ ቱርኮቹን አታለሏቸው፣ መጥፎ ሐር ለሚርቁ፣ ጥሩ ሐር ለሚቀርቡ ሕዝቦች እንሰጣለን በማለት እንዲቀርቡ አታለሏቸውና በየጥቂቱ ተገዥ አደረጓቸው፣ ቱርኮችም ለሀምሳ አመታት ለቻይናውያን ተገዥ ሆኑ። ሆኖም የቢልጌ አባት በአመጽ ቱርኮቹን አስነስቶ ከቻይና አምልጠው ወደ ኦርኾን ተመለሱና እንደገና አሸናፊዎች ሆኑ ይላል።

ትርጉሙ በሙሉ (በእንግሊዝኛ፣ 'texts' ይጫኑ)