Jump to content

የኦርኾን ጽሕፈት

ከውክፔዲያ

የኦርኾን ጽሕፈት ቢያንስ ከ7ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ጥንታዊ ቱርክኛ ለመጻፍ ይጠቀም የነበረ አልፋቤት ነው። ይህ ጥንታዊ ቱርክኛ ቋንቋ በመካከለኛው እስያ የተነገረ ሲሆን የዛሬው ቱርኪክ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባት ነበረ። በዚሁ ጽሕፈት የተጻፈው ጽሑፎችና ቅርሶች በተለይ በሞንጎልያኪርጊዝስታንሳይቤሪያ፣ ምዕራብ ቻይና ወዘተ. ተገኝተዋል፤ እንዲሁም ተመሳሳይ ጽሕፈቶች በምሥራቅ አውሮጳ እስከ ሀንጋሪ ድረስ ታውቀዋል።

የተደረጀው በኡዝቤኪስታን ከተገኘው ሶግዲያን ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። ሌላ ሃልዮ ግን ፊደሎቹ የተለሙ ከቻይናዊ ጽሕፈት እንደ ነበር ይላል። ከቀኝ ወደ ግራ ይነባል።

ጥንታዊ ቱርክኛ አልፋቤት
Using ምልክቱ ትርጉሙ
አናባቢዎች A
I
O
U
ተናባቢዎች harmonized መክፈቻ፦
(¹) — ከ'ኦ' 'ኡ' ጋር
(²) — ከ'አ' 'ኢ' ጋር
ቦ፣ ቡ ባ፣ ቢ
ዶ፣ ዱ ዳ፣ ዲ
ጎ፣ ጉ ጋ፣ ጊ
ሎ፣ ሉ ላ፣ ሊ
ኖ፣ ኑ ና፣ ኒ
ሮ፣ ሩ ራ፣ ሪ
ሶ፣ ሱ ሳ፣ ሲ
ቶ፣ ቱ ታ፣ ቲ
ዮ፣ ዩ ያ፣ ዪ
only (¹) — Q
only (²) — K
Q ቆ፣ ቁ K ካ፣ ኪ
ከማንኛውም አናባቢ ጋር -CH
-M
-P
-SH
-Z
-NG
clusters + vowel ICH, CHI, CH ኢች፣ ቺ፣ ቸ
IQ, QI, Q ኢቅ፣ ቂ፣ ቀ
OQ, UQ,
QO, QU, Q
ኦቅ፣ ኡቅ፣
ቆ፣ ቁ፣ ቅ
ÖK, ÜK,
KÖ, KÜ, K
ኦክ፣ ኡክ፣
ኮ፣ ኩ፣ ክ
+ consonant -NCH -ንች
-NY -ኝ
-LT -ልት፣ -ልድ
-NT -ንት፣ -ንድ
ቃል መለያ none
(-) — ቃል መጨረሻ ብቻ

ምሳሌ፦ — ከቀኝ ወደ ግራ፦

T²NGR²I — transliteration
/ተጝሪ/ — (እግዚአብሔር)
teñri / tanrı — ዘመናዊ ቱርክኛ ጽሑፍ