የኻዛር መንግሥት
Appearance
የኻዛር መንግሥት (የኻዛራውያን ኻጋነት ወይም ኻዛርያ) በከፊል ዘላን የሆነ የቱርኪክ ሕዝብ ግዛት ሲሆን፣ የቀድሞው ኦኖቅ ኻጋናት መንግሥት በቻይናውያን ሥራዊት በ650 ዓም በተሰበረበት ጊዜ፣ ከቅሬቶቹ ከተነሡት በስሜን ካውካሶስ አውራጃ ዋናው ተተኪ ኃይል ሆነ። ኻዛርያ ይህን አውራጅ እስከ 951 ዓም የኪየቫን ሩስ መንግሥት እስካሸነፋቸው ድረስ ይገዛ ነበር።
በ732 ዓም ግድም የኻዛርያ መንግሥት ወደ ተልሙድ አይሁድና ገብቶ የአገሩ መንግሥት ሃይማኖት እንደ ሆነ ይመስላል። ከዚያው በፊት የቱርኮች ጥንታዊ አጓጉል እምነት (የተንግሪ ሃይማኖት) ነበሩ።