Jump to content

የመንግሥት ሃይማኖት

ከውክፔዲያ
(ከመንግሥት ሃይማኖት የተዛወረ)
ዛሬ በዓለሙ የሚገኙት መንግሥታዊ ሃይማኖቶች።
መንግሥታዊ ሃይማኖቶችና ዋና ሃይማኖቶች በየአገሩ የሚያሳይ ሌላ ካርታ

የመንግሥት ሃይማኖት በአንድ መንግሥት ዘንድ የተመሠረተ ሃይማኖት ወይም ይፋዊ እምነት ነው። ይህ ሲባል ግን የተመሠረተው ሃይማኖት መሪዎች የመንግሥቱ መሪዎች አይደሉም፤ እንደዚህ ከሆነ ግን ያው መንግስት «Theocracy» ይባል ነበር። 'የተመሠረተው ሃይማኖት' ማለት በመንግሥት የተደገፈው እምነት ወይም ትምህርት የሚመለከት ነው።

መንግሥት ሃይማኖቱን እስከ ምን ደረጃ ድረስ እንደሚደግፈው በየአገሩ ይለያያል። ከቃል ድገፋ ብቻ እስከ ገንዘባዊ እርዳታ ድረስ ሊሆን ይችላል። በአንዳንድ አገር ውስጥ የሌሎቹ ሃይማኖቶች ተከታዮች ነጻነት ቢያገኙም በሌላ አገር በኩል ግን ሌላ ሃይማኖት ሁሉ ይከለከላል። ወይም ተከታዮቹ ይሳድዳሉ።

በአውሮፓ ውስጥ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስትያናት በ16ኛ ክፍለ ዘመን ሲወዳደሩና ሲተጋገሉ፤ መንግሥታት የመሪዎቻቸውን ምርጫ ተከተሉ፤ ይህም መርኅ በአውግስቡርግ ውል (1547 ዓ.ም.) ጸደቀ። የእንግሊዝ ንጉሥ በ1525 ዓ.ም. የፕሮቴስታንት እምነት ስለ አጸደቀ፤ በፓፓ ፈንታ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ላይኛ መሪ እሱ ሆነ። በስኮትላንድ ግን በመቃወም የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ሆነ።

አንዳንዴ፣ አንድ አገር ወይም ክፍለሀገር ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች በገንዘብ ይደግፋል። ለምሳሌ በፈረንሳይ ውስጥ በአልሳስ-ሞዘል ጠቅላይ-ግዛት እንዲሁም በጀርመን አገር እንዲህ ይደረጋል።

በአንዳንድ ኮሙኒስት አገር በተለይ በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፤ መንግስት አንዳንድ ሃይማኖት ድርጅት ብቻ ይፈቀዳልና ሌሎቹ አይፈቀዱም። እንደነዚህ ባሉት አገሮች የተመረጠው ትምህርት ወይም እምነት የማርክስ ወይም የማው ጸ-ቱንግ ጽሑፎች ይሆናል።

ከመመሠረት መነቀል (Disestablishment)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከመመሠረት መነቀል (Disestablishment) ማለት አንድ ሃይማኖት ወይም ቤተ ክርስቲያን የመንግስት አካል ከመሆን የሚቋረጥበት ሂደት ነው። ለምሳሌ በእንግሊዝ አገር በመጨረሻ 19ኛ ክፍለ ዘመን እንዲህ ለማድረግ የታገለ እንቅስቃሴ ቢኖርም አልተከናወነምና መቸም አልሆነም። በአይርላንድ ግን የአይርላንድ ቤተ ክርስቲያን1863 ዓ.ም. ከመመሠረት ተነቀለ። በ1912 ዓ.ም. ደግሞ በዌልስ ውስጥ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ከመመሠረት ተነቀለ።

አሜሪካ ሕገ መንግሥት (1ኛ የሕግ መለወጫ፣ 1783 ዓ.ም.) መሠረት ምንም ሃይማኖት እንዳይመሠረት በግልጽ ይከለከላል። ከዚህም ጋር መንግስት በሃይማኖቶች ጉዳይ ጥልቅ ከማለት ይከለከላል። ሆኖም የተወሰነ ክፍላገር መንግሥት የተመሠረተ ሃይማኖት ከመኖር አይከለክልም። ለምሳሌ ኮነቲከት እስከ 1810 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቤተ ክርስቲያን ነበረው፤ ማሳቹሰትስም እስከ 1825 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቤተ ክርስቲያን ነበረው።

ዛሬ የአሜሪካ ክፍላገሮች ሁሉ ለኗሪዎቻቸው የሃይማኖት ነጻነት ያረጋግጣሉ። ከነዚህም መካከል 8ቱ እነሱም አርካንሳውሜሪላንድ፣ ማሳቹሰትስ፣ ስሜን ካሮላይናፔንስልቬኒያደቡብ ካሮላይናተነሲቴክሳስ፤ እምነተ ቢስ ሰው ከመሾም ቢከለክሉም ይህ አይነት ሕግ ግን አሁን (ከ1953 ዓ.ም. ጀምሮ) ተግባራዊ ሆኖ አይቆጠረም።

ክርስቲያን አገሮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሚከተሉት መንግስታት የክርስትና ቤተ ክርስቲያን ዓይነት በየአይነቱ መሠርተዋል።

  • ዛምቢያ በ1983 ዓም ሕገ መንግሥት መሠረት «ክርስቲያን አገር» ነው።

እነዚህ አገራት ወይም ክፍላገራት የሮማ ካቶሊክ ሃይማኖት በይፋ አላችው።


*(ከተሐድሶ እና ከጥንታዊ ካቶሊክ ጋር)
**(ከተሐድሶ ጋር)

ምስራቅ ኦርቶዶክስ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እነዚህ መንግሥታት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አይነት በይፋ አሏቸው።


*(ከሉተራን ጋር)

እነዚህ መንግሥታት የሉተራን ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አላቸው።


*(ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ ጋር)

ይህ መንግሥት የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አለው።

ተሐድሶ (ሪፎርምድ)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እነዚህ መንግሥታት የተሐድሶ ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አላቸው።


*(ከሮማ ካቶሊክ እና ከጥንታዊ ካቶሊክ ጋር)
**(ከሮማ ካቶሊክ ጋር)

ጥንታዊ ካቶሊክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እነዚህ መንግሥታት 'ጥንታዊ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን' የተባለው አይነት በይፋ አላቸው።

  • ስዊስ አገር እነዚህ ክፍላገራት ('የስዊስ ክርስቲያን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን') ፦
    • አርጋው
    • ባዘልቤት
    • በርን

(በነዚህም 3 ውስጥ የሮማ ካቶሊክና የተሐድሶ አይነቶች አብረው ይፋዊ ናቸው)

የእስላም አገሮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሚከተሉት መንግስታት የእስልምና ዓይነት በይፋ መሠርተዋል።

የቡዲስት አገሮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሚከተሉት መንግስታት የቡዳ ሃይማኖት ዓይነት በይፋ መሠርተዋል።

  • ቡታን ('ድሩክፓ ካግዩ' ቲቤታዊ አይነት)
  • ካምቦዲያ ('ጤራቫዳ' አይነት)
  • ሩስያ ውስጥ የሆነ ክፍላገር፦
  • ስሪ ላንካ (ጤራቫዳ አይነት - ልዩ ሁኔታ እንጂ 'መንግስታዊ ሃይማኒት' አይባልም
  • ታይላንድ (ጤራቫዳ አይነት) - ልዩ ሁኔታ እንጂ 'መንግስታዊ ሃይማኖት' አይባልም

ሕንዱ አገራት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከአገራት ኔፓል ብቻ የሕንዱ ሃይማኖትን በኦፊሴል ይዞ ነበር። በ1998 ዓ.ም ግን፣ በአመጻዎች ችግር ምክንያት ይህ ሁኔታ ተለውጦ እምነቱ ከመመሰረት ተነቀለ።

እስራኤል ሕገጋት መሠረት አገሩ 'የአይሁድ አገር' ይባላል። ይሁንና 'አይሁድ' የሚለው ቃል ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን አንድ ዘር ወይም ወገን ማለት ደግሞ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አይሁድና ምን ማለት እንደሚሆን ለአገሩ ክርክር ሆኗል። አሁን እስራኤል አንዳንድ ተቋም በተለይም የኦርቶዶክስ አይሁድ ተቅዋማት ይደግፋል፤ ከዚህም በላይ የኦርቶዶክስ አይሁድ፣ የእስላም፤ የክርስቲያንና የድሩዝ ችሎቶች ይፈቅዳል።

በጥንት ሱመር መንግሥታት የመንግስት ሃይማኖት ጽንሰ ሀሣብ ይታወቅ ነበር። እያንዳንዱ ከተማ-አገር ወይም ሕዝብ የራሱን አማልክት ወይም ጣኦት ይኖሩት ነበር። የድሮ ሱመር አለቆች ብዙ ጊዜ የከተማቸውን አምላክ ያገለገሉ ቄሶች ማዕረግ ደግሞ ነበራቸው። በኋላ ዘመን እንዲሁም የባቢሎንና የአሦር መንግሥታት ሃይማኖት አረመኔ ነበር።

ጥንታዊ ግብጽ መንግሥት ሃይማኖት እንደ መስጴጦምያ ባሕል በብዙ አማልክትና ጣኦት ያመነ አረመኔነት ነበር። ንጉሥ ወይም ፈርዖን በመጀመርያ እንደ አምላካቸው ሔሩ ትስብዕት ይቆጠር ነበር፣ በኋላ ሌሎችም አማልክት ከዘመን ወደ ዘመን ይመርጡ ነበር። ከ1357 እስከ 1338 ዓክልበ ድረስ የፀሐይ ጣዖት አተን አምልኮት ብቻ ወይም ሞኖቴይስም የግብጽ መንግሥት ሃይማኖት ሆነ፤ ከዚያ ወደ በፊቱ ፖሊቴይስም እምነት ተመለሰ።

እስራኤል አስተያየት ከጎረቤቶቿ ከባብሎን ከግብጽና ከግሪክ ባህሎች እጅግ ተለየ። ቅዱስ መጻሕፍታቸው እንደሚገልጹ፣ እምነታቸው በአንድ አምላክ ድርጊቶች በታሪካዊ ዜና መዋዕል ውስጥ የጸና እንጂ እንደ ጎረቤቶቿ በልዩ ልዩ አማልክት አፈ-ታሪካዊ ዠብዱዎችና ውድድሮች አልተመሠረተም ነበር። እነዚህ መጻሕፍት የዛሬው ብሉይ ኪዳን (ታናክ) ናቸው።

ሰዎቹ በብዙ አማልክት ቢያምኑም እያንዳንዱ ጥንታዊ ግሪክ ከተማ የገዛ ዐቃቤ አምላኩ ነበረው። እንዲሁም የአቴና አምላክ አቴና ነበረች፤ የስፓርታም አርቴሚስ፣ የዴሎስ አፖሎ፣ የኦሊምፒያ ዜውስ ነበሩ።

ከጥንት ጀምሮ በሮማውያን አረመኔ እምነት ገዢዎቹ የሲቢሊን መጻሕፍትን እንደ ቅዱሳን ጽሑፎች ለትንቢቱ ይመከሩ ነበር።

ሮማ መንግሥትአውግስጦስ ጀምሮ ላይኛ ቄስ የተባለው ቄሳር ወይም ንጉሡ ነበረ። ብዙ ጊዜ ንጉሡ በትእቢቱ ብዛት እኔ አምላክ ነኝ በግልጽ ያዋጅ ነበር። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ ለንጉሡ ካልጸለዩ ይሙት በቃ በሕዝብ ላይ ደረሰባቸው። በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖችና አይሁዶች ለሮማ ንጉስ አንጸለይም ብለው ተገደሉ።

በ303 ዓ.ም. ንጉሡ ጋሌሪዎስ አልጋ ላይ ወድቆ ትንሽ ሊያርፍ ሲል በመንግሥቱ ግዛት ውስጥ ላሉት ክርስቲያኖች ሁሉ ይቅርታ ሰጠ። ከዚህ በፊት የክርስትናን ሃይማኖት ለማጥፋት በሙሉ ሞክሮ ነበር። ከዚያ ሁለት የጋርዮሽ ቄሣሮች 1ኛ ቆስጠንጢኖስ እና ሊቂኒዎስ305 ዓ.ም. የሚላኖ አዋጅን አወጡ። ይህ ህግ ለሰው ሁሉ የሃይማኖት ነጻነት በማረጋገጥ የክርስቲያኖች መሬት ያለ ገደብ እንዲመልስላቸው የሚያዝዝ ነበር።

317 ዓ.ም. ቆስጠንጢኖስ የኒቂያ ጉባኤ ጠሩ። ቢባልም ለብዙ አመታት ከዚህ በኋላ በጥምቀት እንዳልገቡ መገንዘብ ይረዳል። አሁን ክርስትና በሮማ ውስጥ በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆን በብዙዎች ሕዝብ በግልጽ ይከተል ጀመር። በዚህ ዘመን አካባቢ ግን የሮማ መንግሥት ጎረቤቶች የነበሩት የአክሱም መንግሥትና አርሜኒያ ከነገስታታቸው ጥምቀት አንስቶ በይፋ ወደ ክርስትና ገብተው ነበር።

ለጥቂት ጊዜ ከ353 እስከ 355 ዓ.ም. ድረስ የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ መንግሥቱን ወደ ድሮ አረመኔ እምነት መለሠው። ተከታዩ ግን ክርስቲያን በመሆኑ አገሩን ወደ ክርስትና ፕሮግራም መለሰ።

በመጨረቫ በ372 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በንጉሡ 1ኛ ቴዎዶስዮስ አዋጅ መሠረት የሮማ መንግስት ሃይማኖት በይፋ ተደረገ።

ሳሳኒድ መንግሥት (218-643 ዓ.ም.) ይፋዊ ሃይማኖት የዞራስተር (ዛራጡሽትራ) ሃይማኖት ነበር። ፋርስ ከ643 ዓም ጀምሮ እስላማዊ ሲሆን በስሜን በቀድሞው ሂርካኒያ በኋላ ታባሪስታን በተባለው ክፍላገር በጥቃቅን መንግሥታት መኃል፣ የዞራስተር እምነት እስከ 1399 ዓም ድረስ በይፋ ተቀጠለ።

አዲያቤኔ የተባለ በስሜን ሜስጶጦምያ የነበረ ሌላ ትንሽ መንግስት ደግሞ በ26 ዓ.ም. አይሁድናን ተቀበለ። ጎረቤታቸውም በሶርያ የተገኘው የኦስሮኤና መንግሥት በዚያን ጊዜ ክርስትናን እንደ ተቀበለ ይባላል።

ሕንድ አገር የሠፈሩት ሕዝቦች በብዛት ድራቪዳውያንአርያኖች ሲሆኑ፣ እነዚህም መጀመርያ የየራሳቸውን እምነቶች ቢኖራቸውም፣ ሁለቱ በታሪክ ላይ ከመቀላቀላቸው የተነሣ አንድላይ የሂንዱ ሃይማኖት ሠርተዋል። በሕንድ አገሮች ከጥንት ጀምሮ የቄሳውንት መደብ ወይም ብራህማኖች የተከበሩ ባለሥልጣናት ነበሩ።

በኋለኛ ዘመን የአንዳንድ ብሔር ገዢ ለአዳዲስ ሃይማኖቶች ቡዲስምጃይኒስም ተከታዮች ሆኑ። በጎታማ ቡዳ ሕይወት ዘመን የማጋዳ መንግሥት ንጉሥ ቢምቢሳራ (550-500 ዓክልበ. ግድም የገዛ) የቡዳ ምእመን እንደሆነ ይባላል፤ ሆኖም በጃይኒስም ዘንድ ይሄው ንጉሥ የጃይኖች አስተማሪ የማሃቪራ ተከታይ ነበር እንጂ። የማጋዳ ገዦች ከዚያ ወይም ቡዲስም ወይም ጃይኒስም እንደ ደገፉ ግልጽ ባይሆንም፣ በሚከተለው ማውርያ መንግሥት ንጉሦቹ መጀመርያ (ከ330 ዓክልበ. ጀምሮ) የሕንዱ (ብራህማኒስም) ደጋፊዎች ይመስላሉ። መጀመርያው ማውርያ ንጉሥ ቻንድራጉፕታ የጃይን ተከታይ እንደ ሆነ ዙፋኑን ለልጁ ቢንዱሳራ ተወ፤ ቢንዱሳራ ግን አጂቪካ የተባለውን የሕንዱ ፍልስፍና ደጋፊ ነበር። በቢንዱሳራ ልጅ አሾካ ዘመን የአሾካ አዋጆች ከ264 ዓክልበ. ጀምሮ ቡዲስምን በሕንድ የመንግሥት ሃይማኖት አደረገው። ነገር ግን ከ232- 210 ዓክልበ. የገዙት ተከታዮቹ እንደገና የጃይኒስም ደጋፊዎች ነበሩ። ከ193 ዓክልበ. በሚከተለው ሹንጋ መንግሥት ግዛቱ ከቡዲስም ወደ ሒንዱ ሃይማኖት ተመለሠ። በዚህ ዘመን ደግሞ የካሊንጋ ገዢዎች በተለይም ኻራቬላ (100 ዓክልበ. ግድም) የጃይኒስም ደጋፊዎች እንደ ነበሩ ይመስላል።

በኋላ በሕንድ ከነበሩት የጃይኒስም መንግሥታት፣ ምዕራብ ጋንጋ ከ300-1000 ዓም ግድም፣ ካናውጅ 740-825 ዓም ግድም፣ ራሽትራኩታ 806-870 ዓም፣ ሆይሳላ 1018-1100 ዓም፣ እና ጉጃራት ከ1144-1164 ዓም ይጠቀሳሉ።

እንደገና በስሜን ከ598 እስከ 637 ዓም በሕንድ የገዛ ንጉሥ ሃርሻ ቡዲስምን ደገፈ። ከዚያ ከ742 እስከ 1150 ዓም ግድም የቆየው የፓላ መንግሥት ደግሞ ቡዲስት ነበረ። ይህ በሕንድ መጨረሻው ቡዲስት መንግሥት ነበር።

ከ1183 ዓም ጀምሮ እስላም መንግሥታት በጥልቅ ወደ ሕንድ አገር ወርረው በተለይ የደልሂ ሡልታናት (1198-1518 ዓም) እና የሙጋል መንግሥት (1518-1849 ዓም) በሠፊው በሕንድ ገዙ። ከ1666-1810 ዓም የገዛው የማራጣ መንግሥት የሒንዱ መንግሥት ነበረ። በተጨማሪ ከ1791 እስከ 1841 ዓም ድረስ በፑንጃብ አካባቢ የኖረው ሲኽ መንግሥት በአዲሱ ሲኽ ሃይማኖት ተጀመረ። በ1800ዎቹ ዓም እነዚህ ሁሉ በእንግሊዞች ተሸንፈው ሕንድ አገር ለጊዜው የዩናይትድ ኪንግደም ቅኝ አገር ነበረች፤ ከ1939 ዓም ጀምሮ ነጻንቱን አገኝቶ በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ባይኖርም የሂንዱ ሃይማኖት ይደገፋል።

በጥንታዊው ዘመን የቻይና እምነት የወላጆችና አያቶች አምልኮትና ሻማኒስም ነበረ። ፈላስፋው ኮንፉክዩስ (ወይም ኮንግፉጸ፣ 559-487 ዓክልበ.) የመሠረተው እምነት ወይም ፍልስፍና ከ148 ዓክልበ. ጀምሮ በይፋ በሃን ሥርወ መንግሥት ተከተለ። ወደ ማዕረግ ለመሾም ዕጩዎቹ በዚህ እምነት መጻሕፍት ይፈተኑ ነበር።

በዚህ መንግሥት መጨረሻ (212 ዓ.ም.) ከተከተሉት ተወዳዳሪ ክፍላገራት መሃል፣ አንዳንዱ የሌላ ቻይናዊ ሃይማኖት የዳዊስም ደጋፊ ነበረ፤ በተለይ ከ207 እስከ 252 ዓም የነበረው ወይ መንግሥትና ከ416 እስከ 444 ዓም ድረስ ስሜን ወይ በይፋ ዳዊስት መንግሥታት ነበሩ። ከዚያ በኋላ ግን ስሜን ወይ ወደ ቡዲስም ተለወጠ። በደቡቡ ቻይና ደግሞ ንጉሦች ዉ ልያንግ ከ509-541 ዓም እና ዉ ቸን 549-551 ዓም በተለይ ቡዲስቶች ነበሩ። መላው ቻይና በ571 ዓም በሱዊ ሥርወ መንግሥት እንደገና ሲዋሀድ የመንግሥት ሃይማኖት ቡዲስም ሆነ። የሚከተለው ታንግ ሥርወ ነግሥት ግን ከ610-682 እና ከ697-899 ዓም ወደ ዳዊስም ተመለሠ፤ ከ682-697 ዓም የገዛች ንግሥት ግን ቡዲስት ነበረች።

ከዚህ በኋላ በልያው ሥርወ መንግሥት 899-1117 ዓም፣ ጂን ሥርወ መንግሥት 1107-1226 ዓም፣ በምዕራብ ሥያ 1030-1219 ዓም እና የሞንጎሎች ንጉሥ ኩብላይ ኻን በመሠረተው ይዋን ሥርወ መንግሥት ውስጥ (1261-1360 ዓም) ቡዲስም እንደገና የመንግሥት ሃይማኖት ሆነ። ከ1360 እስከ 1903 ዓም ድረስ የነበሩት መንግሥታት እንደገና የኮንፉክዩስን ትምህርት ደገፉ፤ ከ1903 ዓም ጀምሮ እስካሁን የነበሩትም ከተመሠረተ ሃይማኖት ተነቅለዋል።

ቲቤትየቲቤት መንግሥት ጥንታዊው ኗሪ እምነት «ቦን» የሚባል ሃይማኖት ሲሆን፣ በተለይ ከ610-642 ዓም፣ ከ753-832 ዓም እና ከ950 ዓም ጀምሮ ቡዲስት ነበር።

ጃፓን ድሮ መንግሥት ሃይማኖት ሺንቶ ሲባል በ579 ዓም የጃፓን መንግሥት ቡዲስም ደግሞ ተቀበለ። ሁለቱ ሃይማኖቶች ሲደገፉ በብዙ ታሪካዊ ረገዶች ይቀላቅሉ ነበር። ከ1860 እስከ 1937 ዓም ግን የመንግሥት ሃይማኖት ሺንቶ ብቻ ተደረገ፤ የቡዲስም ተጽእኖ ለማስወገድ እርምጃ ወሰደ። ከ1937 ዓም ጀምሮ የምንግሥት ሃይማኖት ባይኖርም፣ ሺንቶና ቡዲስም እስካሁን በሕዝቡ ዘንድ ዋና እምነቶች ሆነው ቆይተዋል።

የክርስትና መስፋፋት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እስከ 1450 ዓ.ም. ድረስ ክርስትና ይፋዊ የሆነበት ጊዜ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የዓለም መንግሥት ሃይማኖቶች በ812 ዓም

ከ1450 ዓ.ም. በኋላ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአውሮፓ ውስጥ ያሉት መንግሥታት ሃይማኖቶች ወይም ቀድሞ የነበሯቸው ሃይማኖቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ሀገር ሃይማኖት አይነት ከመመሰረት የተነቀለበት አመተ ምኅረት
አልባኒያ1 ከነጻነት ጀምሮ የለም
አንዶራ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
አንሃልት (ጀርመን) የአንሃልት ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
አርሜኒያ የአርሜንያ ሃዋርያዊ ቤተክርስቲያን ተዋሕዶ 1913
ኦስትሪያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1910
ባደን (ጀርመን) ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና የባደን ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ካቶሊክና ሉተራን 1910
ባየርን (ጀርመን) ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1910
ብሩንዝቪግ-ሊውነቡርግ (ጀርመን) የብሩንዝቪግ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ቡልጋሪያ የቡልጋርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1938
ቆጵሮስ የቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ አልተነቀለም
ቼኮስሎቫኪያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1912
ዴንማርክ የዴንማርክ ቤተክርስቲያን ሉተራን አልተነቀለም
እንግሊዝ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን አንግሊካን አልተነቀለም
ኤስቶኒያ የኤስቶኒያ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1932
ፊንላንድ2 የፊንላንድ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን ሉተራን 1911
ፈረንሳይ3 ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1897
ጂዮርጂያ የጂዮርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1913
ግሪክ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ አልተነቀለም
ሄሰ (ጀርመን) የሄሰ እና የናሶ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሀንጋሪ4 ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1840
አይስላንድ የአይስላንድ ቤተክርስቲያን ሉተራን አልተነቀለም
አይርላንድ የአይርላንድ ቤተክርስቲያን አንግሊካን 1863
አየርላንድ ሪፑብሊክ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1965
ጣልያን ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1976
ሊክተንስታይን ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ሊፐ (ጀርመን) የሊፐ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ 1910
ሊትዌኒያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1932
ሊውበክ (ጀርመን) ስሜን እልባዊ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሉክሳምቡርግ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ማልታ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ሜክለንቡርግ (ጀርመን) የሜክለንቡርግ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሞናኮ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ሆላንድ የሆላንድ ተሐድሶ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ 1787
ኖርዌ የኖርዌ ቤተክርስቲያን ሉተራን አልተነቀለም
ኦልደንቡርግ (ጀርመን) የኦልደንቡርግ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ፖላንድ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1931
ፖርቱጋል ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1902
ፕሩሲያ (ጀርመን) 13 የጀርመን ወንጌላዊ አብያተ ክርስትያናት ሉተራን 1910
ሮማኒያ የሮማኒያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1939
ሩሲያ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1909
ጦሪንገን (ጀርመን) የጦሪንገን ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሳክሰን (ጀርመን) የሳክሰን ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሻውምቡርግ-ሊፐ (ጀርመን) የሻውምቡርግ-ሊፐ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ስኮትላንድ የስኮትላንድ ቤተክርስቲያን ፕሬስቢቲሪያን አልተነቀለም
ሰርቢያ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1935
እስፓንያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1970
ስዊድን የስዊድን ቤተክርስቲያን ሉተራን ጥር 1992
ቱርክ እስልምና 1920
ቫልደክ (ጀርመን) የሄሰ-ካሰልና የቫልደክ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ዌልስ የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን አንግሊካን 1910
ቩርተምበርግ (ጀርመን) የቩርተምበርግ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910

^1:  በ1959 ዓ.ም. የአልባኒያ መንግስት በይፋ ከሃዲነት «የመንግስት ሃይማኖት» አደረገና ሃይማኖቶች ሁሉ ከለከለ። ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ቆየ።

^2:  የፊንላንድ ብሔራዊ ቤተክርስቲያን እስከ 1801 ዓ.ም. ድረስ የስዊድን ቤተክርስቲያን ነበረ። ከ1801 እስከ 1909 ዓ.ም. ድረስ ፊንላንድ የሩስያ ቅኝ አገር ስትሆን የተለየ የፊንላንድ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን በሩሲያ መንግስት በፊንላንድ ተመሰረተ። በ1911 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት መሠረት ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የጋርዮሽ ብሔራዊ ቤተክርስቲያን ነው።

^3:  በፈረንሳይ ውስጥ በ1793 ዓ.ም. ስምምነት መሠረት የሮማ ካቶሊክ፣ የካልቪናዊ፣ የሉተራንም ቤተክርስቲያኖች እንዲሁም አይሁድና ሁሉ በመንግሥት የተደገፉ ሆኑ። በ1897 ዓ.ም. መንግሥት ከሃይማኖት ግን ተለየ።

^4:  በሀንጋሪ የ1840 ሕገ መንግሥት መሠረት አምስት የጋርዮሽ አብያተ ክርስቲያናት ተመሰረቱ፤ እነሱም የሮማ ካቶሊክ፣ የካልቪናዊ፣ የሉተራን፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስና የዩኒታሪያን ቤተክርስቲያኖች ናቸው። በ1887 ዓ.ም. አይሁድና ስድስተኛ የተምሰረተ እምነት ሆነ። በ1940 ዓ.ም. ግን የሀንጋሪ መንግሥት ሃይማኖቶቹን ሁሉ መለየት ተወ።