Jump to content

ሱቁጥራ

ከውክፔዲያ
የሱቁጥራ ሥፍራ
ድሮ ስለቀይ ፈሳሹ ተፈላጊ የነበረ የሱቁጥራ ሜርቆ

ሱቁጥራ ወይም ሶኮትራ (አረብኛ፦ سُقُطْرَى) በሕንድ ውቅያኖስ የሚገኝ የየመን ደሴት ነው። ባካባቢው ሦስት ሌሎች ትንንሽ ደሴቶችም አሉ።

የሱቁጥራ ስም መነሻ ከሳንስክሪት /ድቪፐ ሱቀደረ/ «ሀሤት ደሴት» እንደ መጣ ይባላል። በ1ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈው ግሪክኛ የቀይ ባሕር ፔሪፕሉስ (ጉዞ መግለጫ)፣ ደሴቱ /ዲዮስኮሪዶ/ ወይም «የዲዮስኮሪ» (መንታ ጣኦታት) ተባለ። ሦስተኛው መነሻ አረብኛው /ሱቅ አል-ቃትራ/፣ «የጠብታ ሱቅ» እንደ ሆነ ይባላል። ጠብታ ማለት በሱቁጥራ ብቻ የሚገኘው የሱቁጥራ ሜርቆ ቀይ ፈሳሽ ሲሆን፣ ይህ ፈሳሽ ስለቀይ ቀለሙ ለማጌጥ ተፈላጊ ነበር።

በጥንት የብዙ አገራት መርከበኞች እንደ ደረሱ ከጽሑፎቻቸው ብዛት ታውቋል። የደሴቱ ኗሪዎች በ44 ዓም በቅዱስ ቶማስ ተጠምቀው ወደ ክርስትና እንደ ገቡ ይነገራል። የኔስቶራዊ ቤተ ክርስቲያን ክፍልፋይ ምዕመናን ሆኑ። ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ፣ በአሁኑ የመን የተገኘው ማህራ ሱልጣናት ሱቁጥራን ይገዙ ነበር። በ1499 ዓም የፖርቱጋል ጦር መርከቦች ሱቁጥራን ያዙት፣ ስላልተስማማቸው ግን በ1503 ዓም እንደገና ተዉት። ጥቂት ኔስቶራዊ ክርስቲያን ሕዝብ በሱቁጥራ እስከ 1792 ዓም ድረስ ቀሩ።

የዛሬው ኗሪዎች አረብኛ እንደ መደበኛ ቋንቋ ከመናገራቸው በላይ፣ ኗሪ ቋንቋቸው ሱቁጥርኛ እንደ ደቡብ አረብኛ አይነት የሆነ ሴማዊ ቋንቋ ነው። ዋና ምርቶቻቸው ተምርንጥር ቅቤትምባሆአሣ ናቸው። የበሬና የፍየልም እረኞች አሉ።

ደሴቱ ከአሕጉር በመገለሉ፣ በርካታ በሱቁጥራ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ አትክልትእንስሳት ዝርዮች አሉበት። በተለይም

ከአትክልት፦

ከእንስሳት፦