Jump to content

ማልዲቭስ

ከውክፔዲያ
(ከማልዲቭስ ደሴቶች የተዛወረ)

ማልዲቭስ ሪፐብሊክ
Dhivehi Raa'jeyge Jumhooriyya

የማልዲቭስ ሰንደቅ ዓላማ የማልዲቭስ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ክኣኡሚኢ ሳሏም

የማልዲቭስመገኛ
የማልዲቭስመገኛ
ዋና ከተማ ማሌ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ማዲቭኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
 
ዓብዱልላ ያሜን
ዓብዱልላ ጂሃድ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
298 (187ኛ)
0
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
393,253 (175ኛ)
ገንዘብ ሩፊዯ
ሰዓት ክልል UTC +5
የስልክ መግቢያ +960
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .mv


ማልዲቭስሕንድ ውቅያኖስ የተገኘ የደሴቶች አገር ሲሆን ዋና ከተማው ማሌ ነው። ለሕንድስሪ ላንካ አገራት ይቀርባል። 400 ሺህ ያሕል ኗሪዎች አሉት።

የማልዲቭ ሕዝብ መጀመርያ ከሰሜናዊ ሕንድ ደረሱ፣ ቋንቋቸው ዲቬሂኛ ይባላል። ይህ የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋ ስለሆነ በውኑ የእንግሊዝኛ ዘመድ ነው። እንደ አረብኛ ፊደል በሚመስል ልዩ ጽሕፈት ይጻፋል።

በማልዲቭዝ ለሚኖሩ ሰዎች ከእስልምና በቀር ሌላ አምልኮት አይፈቀድም። የደሴቶቹ ሕዝብ አስቀድሞ የሕንድ ሃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ ከዚያ ለጊዜ የቡዲስም አማኞች ሆኑ። በመጨረሻ በ1145 ዓ.ም. እስላሞች ሆኑ።

1879 ዓ.ም. ጀምሮ ሡልጣናቸው በብሪታንያ ጥብቅና ሥር ይቆይ ነበር። በ1957 ዓ.ም. ከብሪታንያ ነጻ ሆነ፣ በ1960 ዓ.ም. ሪፐብሊክ ሆነ። በ1980ዎቹ 3 መንፈቅለ መንግሥት ሙከራዎች ቢሆኑም አልተከናወኑም። በ1996 ዓ.ም. ከታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ በኋላ አንድ ትላቅ ጐርፍ በማዲቭስ ደሴቶች ላይ ብዙ ጉዳት አደረገ። የዓለም ውቅያኖሶች መጠን በዓለማዊ መሞቅ ከፍ ከፍ እያለ፥ ምናልባት በመቶ አመት ውስጥ ማልዲቭስ ምንም ኗሪዎች የማይኖሩባቸው ደሴቶች እንዳይሆኑ የዕውነት ተግሳጽ አለ። ስለዚህ ነው ከዓለም አገራት ማልዲቭስ የካርቦን ማገዶነት ለመከልከል መጀመርያው አገር የሆነው።

ከ1964 ዓም ጀምሮ ቱሪስም የሀገሩ ምጣኔ ሀብት ዋና ዓምድ ሆኖ በየዓመቱ 500 ሺህ ቱሪስቶች ይጎበኛሉ። ከደሴቶቹ አንዳንድ በተለየ ለሆቴል ብቻ ተለይተዋል። እንዲሁ ሲሆን ቱሪስቶቹ የማልዲቭስ ኗሪ ዜጎች በመኖርያዎቻቸው ላይ ከቶ አይደርሱም።

በርካታ የሙዚቃ አይነቶች ከማዲቭስ ይገኛሉ፣ ከነርሱም ውስጥ ቦዱቤራ እና ጣራ የተባሉ ሙዚቃ አይነቶች አሉ። ከነዚህም ጋር የተለመዱ ጭፍራዎች ይሄዳሉ።