የወልወል ጦርነት
Appearance
በኦጋዴን ክልል በኢትዮጵያ እና በኢጣልያዊ ሶማልያ ያለውን ድንበር እንዲያሠምሩ የተላኩት የብሪታንያ እና የኢትዮጵያ ልዑካን በዚሁ ክልል ውስጥ ለሥራ ይዘጋጁ ነበር። በዚህ ጊዜ ‘ሙስቲ’ በሚባል የኢጣልያ መቶ ዓለቃ የሚታዘዙ ሁለት መቶ ሶማሌያዊ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው፤ ከሺህ በላይ የውሐ ጉድጓዶች የነበሯትን፤ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ያለችውን ወልወልን ከበዋት ተገኙ። በወቅቱ የኦጋዴን ገዥ የነበሩት የፊታውራሪ ሺፈራው ወታደሮችና የኢጣልያን ወገን በሚመራው በሻለቃ ቺማሩታ ወታደሮች ለሁለት ሣምንታት ከተፋጠጡ በኋላ በኢትዮጵያና በፋሽስታዊ ኢጣልያ መካከል ለአምሥት ዓመታት የተከተለው ጦርነት ክብሪት ተጫረ። [1]
== ማጣቀሻ ==
- ^ Mockler, Anthony, “Haile Selassie’s War” (2003), p 37-39