Jump to content

ጊቦን

ከውክፔዲያ
(ከየጊቦን አስተኔ የተዛወረ)
?ጊቦን
ጊቦን ወንድና ሴት ጥንድ
ጊቦን ወንድና ሴት ጥንድ
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ሰብአስተኔ
አስተኔ: ጊቦን
ወገን: 4 ወገኖች
ዝርያ: 18 ዝርያዎች

ጊቦን (Hylobatidae) የጦጣ አስተኔ ነው። በደቡብ-ምሥራቅ እስያ የሚገኙ አራት ወገኖችና 18 ዝርዮች ናቸው።

ከለሎች ጦጣዎች (ቺምፓንዚጎሪላኦራንጉታን) ይልቅ አነስተኛ ናቸው። ጸጉራቸው ነጭ ወይም ጥቁር ሲሆን እንደ ዝርያ፣ እንደ ጾታ ወይም እንደ እድሜ ይለያል። ስለዚህ በብዙ ዝርዮች የጊቦን ወንድና ሴት ምንም አይመሳሰሉም። እንደ ሌሎች ጦጣ አይነቶች ሳይሆኑ፣ ጊቦኖች ባብዛኛው አንድ በአንድ የ«ባልና ሚስት» ጥንዶች ይሠራሉ። አንድ ጊቦን ቤተሠብ አባት፣ እናትና ልጆች በአንዱ ዛፍ ሲቆይ ጧት ጧት አብረው ከፍ ባለ ድምጽ ይጮሃሉ ይዘፍናሉም። በዚህ ዘዴ የጎረቤት ቤተሠብ ሥፍራና ርቀት ማወቅ ይችላሉ። ስለዚህ በጊቦን ቤተሠቦች መካከል ባጠቃላይ ሰላም ይጠበቃል። እንደ ጊቦን ፍጥነት በዛፍ ውስጥ መዞር የሚችል ሌላ እንስሳ የለም።

የሚበሉት በተለይ ፍራፍሬ ሲሆን አንዳንዴ ቅጠል፣ ሦስት አጽቄ፣ ቀይም ዕንቁላል ይጨምራሉ።

ጊቦኖች ደግሞ እስከ 1300 ዓም ያሕል ድረስ በመካከለኛ ቻይና እንደ ተገኙ ይታወቃል። እንዲሁም ሁለት የጠፉት ጊቦን ዝርዮች ቅሪቶች በመካከለኛ ቻይና ተገኝተዋል።