ሰብአስተኔ

ሰብ አስተኔ በጡት አጥቢ መደብ ውስጥ ያለ ክፍለመደብ ነው። በሥነ ሕይወት ጥናት ይህ ክፍለመደብ ሌሙር፣ ዝንጀሮች፣ ጦጣዎችና የሰው ልጅም ይጠቅልላል።
- ሌሙር፣ ጋላጎ፣ ፖቶ ወዘተ. - (አፍሪካና ማዳጋስካር)
- ታርሲየር - (ደቡብ-ምስራቅ እስያ)
- የምዕራብ ክፍለአለም ዝንጀሮች - (አሜሪካዎች)
- የምሥራቅ ክፍለአለም ዝንጀሮች - (አፍሪካና እስያ)፤ አንኮ፣ ጭላዳ፣ ጨኖ፣ ጉሬዛ
- ጦጣ - ጊቦን (እስያ)
በሥነ ባህርይ ረገድ በኩል፣ ከፍጡሮች ሁሉ ቺምፓንዚ የተባለው ጦጣ በሁለት ዝርዮች (ሐለስትዮ እና ሐለስት) ተመድቦ ሲሆን ለሰው ልጅ ቅርብ ዝምድና ያለው ይቆጠራል። ቺምፓንዚ ግን 24 (48) ሐብለ በራሂዎች እያለው፣ የሰው ልጅ 23 (46) ሐብለ በራሂዎች እና ከማናቸውም እንስሳ ይልቅ እጅግ ሃይለኛ አዕምሮ አለው።
ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |