Jump to content

የግምባታ መሬት ሳይንስ በምህንድስና

ከውክፔዲያ

የግምባታ መሬት ሳይንስ በምህንድስና (የአፈር ሜካኒክስ)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአፈር ባህርይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ደግሞ ይዩ፦ ላይ አፈር

በተፈጥሮ አፈር ሶስት ቁሦች አሉት፡ ማለትም ፈሣሽ (ውሃ)፣ ጠጣር አፈር እንዲሁም አየር ናቸው። የአፈር ጥንካሬ በነኝህ ሦስት ቁሶች መጠንና የርስ በርስ ግንኙነት ይወሰናል።

የአፈር ጠጣር ክፍል ከተለያዩ ቁሦች የተሰራ ነው፣ ከነኝህ ውስጥ የሸክላ አፈር (ክሌይ) ፣ አሸዋ፣ የተፈጥሮ ብስባሽ፤ እንዲሁም ከተለያዩ ማእድኖች ይገኙበታል።

እነኝህን የአፈር አይነቶች ለምህንድሥና አላማ በሁለት ይከፈላሉ፣ እርስ በርስ ተጣባቂ አፈሮች (ለምሣሌ የሽክላ አፈር)፣ እርስ በርስ የማይጣበቁ አፈሮች (ለምሣሌ አሸዋ) በተፈጥሮ በመሬት ውስጥ የርስ በርስ ተጣባቂ አፈሮች መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም የአፈርን ባህርይ በከፍተኛ ደረጃ ይወስናሉ።

አፈር በመጠን እንደሚከተለው ይከፋፈላል፤ የሽክላ አፈር (ክሌይ) (<0,006ሚሚ)፣ ዝቃጭ አፈር (ሲልት) (<0,2ሚሚ)፣ አሽዋ (<2ሚሚ)፣ ኮረት (<63ሚሚ)፣ ድንጋይ (>63ሚሚ)