ላይ አፈር
Appearance
ላይ አፈር (ላያፈር፣ ላይኛ አፈር፣ ላይኛፈር) ከምድሩ አፈር ላዕላይ ንብብር ሲሆን ጥልቀቱ ከ5 እስከ 20 ሴንቲሜትር ድረስ ሊሆን ይችላል። ካርቦናዊ ቁስ አካልና ደቂቅ ዘአካል (ጥቅን ሕዋስ) በላይ-አፈሩ ውስጥ በመብዛቱ፣ ስሙ ደግሞ «ሕያው አፈር» ሊባል ይችላል። የምድር ሥነ-ሕይወታዊ ተግባር በብዛት የሚፈጸምበት በዚህ አፈር ንብብር ነው። አትክልት በተለይ ሥሮቻቸውን በእርሱ ሰድደው ንጥረ ምግቦችን ከእርሱ ሊቀበሉ ይችላሉ። ላይ አፈር ከንፋስ ወይም ከጎርፍ የተነሣ ቢጠፋ ኖሮ ብዙ አትክልት በዚያ ለማብቀል አይቻልም።
ላያፈር አለም ዙሪያ በአጸድም ሆነ በእርሻ በሰፊ ይጠቀማል። ልዩ ልዩ አይነቶችም በሱቅ እየተሸቀጡ ነው።