Jump to content

ያኽዱን-ሊም

ከውክፔዲያ
(ከያህዱን-ሊም የተዛወረ)
የያህዱን-ሊም ጽላት

ያኽዱን-ሊምማሪ ንጉሥ ነበረ። ይህ ከ1723 እስከ 1707 ዓክልበ. ግድም ድረስ ነበር። የያጊት-ሊም ልጅና ተከታይ ነበር።

አሞራዊው ያኽዱን-ሊም ግዛቱን እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ በዘመቻ አስፋፋ። ይህን አገር የያዘው ከጠላቶቹ «የያሚና ልጆች» (አካድኛ፦ በን-ያሚና) ነበር። ያሕዱን-ሊም ደግሞ ከያምኻድ ንጉሥ ሱሙ-ኤፑኽ እና ከኤካላቱም ንጉሥ ከ1 ሻምሺ-አዳድ ጋር ይታገል ነበር። በ1720 ዓክልበ. ሻምሺ-አዳድ የአሦር ንጉሥ ሆነ።

ከዓመት ስሞቹ 15 ያህል ታውቀዋል፤ ቀደም-ተከተላቸው ግን ምንም አይታወቅም፦

a - ያህዱን-ሊም ፓሁዳርን የያዘበት ዓመት
b - ያህዱን-ሊም ዛልፓን የያዘበትና የአባቱምን እህል ያቃጠለበት ዓመት
c - ያህዱን-ሊም በያሚና ልጆችና በኢማርአባቱም በር ፊት ያሸነፋቸውበት ዓመት
d - ያህዱን-ሊም የ<...>ን ሥራዊት በተርቃ ያሸነፈበት ዓመት
e - ያህዱን-ሊም ወደ ሄን ሂዶ የያሚና ልጆች ሜዳ ወደ እጁ ያደረሰበት ዓመት።
f - ያህዱን-ሊም የሻምሺ-አዳድ ምድር ሰብል ያቃጠለበት ዓምት
g - ያህዱን-ሊም በያሚና ልጆች በቱቱል በር ፊት ያሸነፋቸውበት ዓመት
h - ያህዱን-ሊም በያሚና ልጆች ያሸነፋቸውበት ዓመት
i - ያህዱን-ሊም የሻማሽ (ጣኦት) ቤተ መቅደስ የሠራበት ዓመት
j - ሁለተኛው ያህዱን-ሊም የሻማሽ ቤተ መቅደስ የሠራበት ዓመት
k - ያህዱን-ሊም በሻምሺ-አዳድ ሥራዊት በናጋር በር ፊት ያሸነፈበት ዓመት
l - ያህዱን-ሊም የፑዙራንን መስኖ የከፈተበት ዓመት
m - ያህዱን-ሊም ወደ ኤካላቱም ምድር የሔደበት ዓመት
n - ያህዱን-ሊም የማሪና የተርቃ ግድግዳዎች የሠራበት ዓመት
o - ያህዱን-ሊም የሑቡር መስኖ የሠራበት ዓመት

በዓመት 'b' የተጠቀሰው «ዛልፓ» በጥቁር ባሕር ላይ በሐቲ የተገኘው ዛልፓ ከሆነ፣ በጥልቅ ወዸ ትንሹ እስያ ገብቶ ነበር ማለት ነው።

በ1707 ዓክልበ. ያኽዱን-ሊም ሻምሺ-አዳድን ሊመታ ሲል በሎሌዎቹ ተገደለ። ሤረኞቹ ሱሙ-ያማንን እየሾሙ የያሕዱን-ሊም ወራሽ ዝምሪ-ሊም ወደ ያምኻድ መንግሥት (አሌፖ) ለጊዤው ሸሸ። ከ፪ ዓመት በኋላ ሻምሺ-አዳድ ማሪን ያዘ፣ በ1694 ዓክልበ. ልጁን ያስማህ-አዳድ የማሪ ንጉሥ አደረገው። ሻምሺ-አዳድ ከሞተ በኋላ ግን በ1687 ዓክልበ. ዝምሪ-ልም ተመልሶ ያስማህ-አዳድን አሸንፎ ወደ ዙፋኑ ተመለሠ።

ቀዳሚው
ያጊት-ሊም
ማሪ ንጉሥ
1723-1707 ዓክልበ.
ተከታይ
ሱሙ-ያማን