Jump to content

ዮንግ ጂ

ከውክፔዲያ

ዮንግ ጂ (ቻይንኛ፦ 雍己) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።

ቀርቀሃ ዜና መዋዕል ዘንድ ለ12 ዓመት ነገሠ። የታይ ገንግ ልጅ ሲሆን ከወንድሙ (ወይም አጎቱ) ሥያው ጅያ ቀጥሎ ነገሠ። የሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦች ደግሞ እንዲህ ይጨምራል፦ «የዪን (ሻንግ) ሥርወ መንግሥት ተጽእኖ ይቀንስ ጀምሮ መሣፍንቱ አንዳንዴ ወደ ጊቢው ሳይመጡ ቸል ይሉ ነበር።»

በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ዮንግ ጂን («ሉ ጂ»ን ብለውት) ከወንድሙ ታይ ዉ በኋላ ያደርጉታል። ታይ ዉ ግን 75 ዓመት ገዛ ሲባል ወንድሙ እንደ ተከተለው የማይመስል ነው።

ቀዳሚው
ሥያው ጅያ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1520-1508 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ታይ ዉ