ታይ ገንግ
Appearance
ታይ ገንግ (ቻይንኛ፦ 太庚) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።
በቀርቀሃ ዜና መዋዕል እና በሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦችም ዘንድ ለ5 ዓመት ከወንድሙ ዎ ዲንግ ቀጥሎ ነገሠ፤ ወንድሙም ሥያው ጅያ ተከተለው። ሆኖም እንዲያውም ዘመኑ ለ25 ዓመት እንደ ቆየ ይታሥባል።
በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ዎ ዲንግን አይጠቅሱትም፤ ታይ ገንግም ከቡ ቢንግ (ዋይ ቢንግ) ቀጥሎ ያደርጉታል።
ቀዳሚው ዎ ዲንግ |
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ 1562-1537 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሥያው ጅያ |