ዋይ ቢንግ
Appearance
ዋይ ቢንግ (ቻይንኛ፦ 外丙) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።
በቀርቀሃ ዜና መዋዕል ዘንድ ለ2 ዓመት፣ በሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦችም ዘንድ ለ3 ዓመት ከአባቱ ታንግ ቀጥሎ ነገሠ፤ ወንድሙም ዦንግ ረን ተከተለው። ዪ ዪን በዚህ ዘመን ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን ቀረ።
ዳሩ ግን በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ዳ ዲንግም እንደ ንጉሥ ይቆጠራል፤ በሌላ ቅደም-ተከተል ይለያያሉ። በዚያው መሠረት ዋይ ቢንግ «ቡ ቢንግ» (卜丙) ተብሎ ከዳ ዲንግና ከበኲሩ ታይ ጅያ ቀጥሎ የታይ ጅያ ወንድም ሆኖ ነገሠ፤ የታይ ጅያም ልጅ ታይ ገንግ ተከተለው። ዋይ ቢንግ ከታይ ጅያ በኋላ ተከተለ የሚሉ ሌሎችም ታሪኮች አሉ። ሆኖም ዳ ዲንግ ሳይነግሥ እንዳረፈ፣ ዪ ዪንም ያለመቋረጥ ከታንግ ጀምሮ እስከ ዎ ዲንግ ድረስ (1628-1581 ዓክልበ.) እንደ ሻንግ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳገለገለ ትክክለኛ ስለሚመስል ቅደም-ተከተሉ ሢማ ጭየን እንዳለው መሆን አለበት።
ቀዳሚው ታንግ |
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ 1600-1597 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ዦንግ ረን |