Jump to content

ዎ ዲንግ

ከውክፔዲያ

ዎ ዲንግ (ቻይንኛ፦ 沃丁) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።

ቀርቀሃ ዜና መዋዕል እና በሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦችም ዘንድ ለ19 ዓመት ከአባቱ ታይ ጅያ ቀጥሎ ነገሠ፤ ወንድሙም ታይ ገንግ ተከተለው። ሢማ ጭየን እንዳለ ዪ ዪን እስከዚህ ዘመን ድረስ የሻንግ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቀረ፣ በዘመኑም ዓረፈ። የቀርቀሃ ዜና መዋዕል ደግሞ ዎ ዲንግ በመጀመርያው ዓመት አዲስ ሚኒስትሩን ጪንግ ሺን ሾመ፣ በ8ኛውም አመት ለዪ ዪን መቃብር ሠዋ ይላል።

ዳሩ ግን በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ዎ ዲንግን አይጠቅሱትም፤ ታይ ገንግም ከቡ ቢንግ (ዋይ ቢንግ) ቀጥሎ ያደርጉታል።

ቀዳሚው
ታይ ጅያ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1581-1562 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ታይ ገንግ