የደም ቧንቧ
Appearance
(ከደም ቧንቧ የተዛወረ)
የደም ቧንቧዎች የሥርዓተ ደም ዝውውር አካል ሲሆኑ ደምን በሙሉ አካል የሚሠራጭባቸው መንገዶች ናቸው። ሶስት ዓይነት የደም ቧንቧ ዓይነቶች አሉ። የመጀመሪያው የደም ቧንቧ ዓይነት ደም ቅዳ ወይም arteriesየሚባለው ሲሆን ደምን ከልብ ወደተለያዩ የሠውነት ክፍሎች የሚወስዱትን የደም ቧንቧዎች የሚወክል ነው። ሁለተኛው ደግሞ ፀጉር ደምስር ወይም ርቂት (capillaries) የሚባሉት ሲሆኑ ደም ከህዋሳቶች ጋር እንዲገናኝ ለተለያዩ ኬሚካላዊ አፀግብሮቶች መንገድ የሚያመቻቹ ናቸው። የሦስተኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ደም መልስ ወይም veins የሚባሉት ሲሆኑ ደምን ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ወደ ልብ የሚመልሱ ቧንቧዎች ናቸው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |