Jump to content

ደረስጌ ማርያም

ከውክፔዲያ
ደረስጌ ማርያም
ደረስጌ ማርያም
ከፍታ 3035 ሜትር
ደረስጌ ማርያም is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ደረስጌ ማርያም

13°01′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°06′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ደረስጌ ማርያም ደባርቅጎንደር ውስጥ ደረስጌ (ደብረ-ስጌ ከሚለው ስም የመጣ)፣እሚባል ቦታ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው። በዘመነ መሳፍንት ገነው የነበሩት ደጃች ውቤ እራሳቸውን ለማንገሥ ሲሉ የጀርመኑን ሠዓሊ እና ሳይንቲስት ዶክተር ሺምፐር በመቅጠር በ1840ዎቹ መጀመሪያ ያስገነቡት ቤተክርስቲያን ነው። በኋላ ላይ ከወደፊት ዓፄ ቴዎድሮስ ጋር በዚሁ አካባቢ ጦርነት ገጥመው ስለተሸነፉ ፣ ራስ ውቤ ለስርዓተ ንግሣቸው ባሠሩት ቤተ ክርስቲያን ዓፄ ቴዎድሮስ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው ዘውድ ጭነው ነገሡበት። ይሄውም በ1847 መሆኑ ነው።

ካርታ