Jump to content

ደብረ ታቦር ሆስፒታል

ከውክፔዲያ

፲፱፻፳፰ ዓ/ም ላይ በልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ አማላጅነት የሰባት ቀን አድቬንቲስት ሚሲዮኖች በደብረ ታቦር ከተማ ሆስፒታል እንዲሠሩ ተፈቀደ። ይህም ከኢትዮጵያ መንግሥት ሰፊ መሬትና ፴ሺ ማሪያ ጠሬዛ ጠገራ ብር የፈጀ ሥራ ነበር። ልዑል ራስ ካሣም ለድሃ ታካሚወች የሚውል ህንጻ በሆስፒታሉ ግቢ እንዲሠራ ከራሳቸው ፲ሺ ማሪያ ጠሬዛ ጠገራ ብር በእርዳታ ሰጡ። የስዊድኑ ጉድሙንድሰንአዲስ አበባ ደብረታቦር አስፈላጊ እቃወችን ጭኖ በገበያ ቀን ደረሰ። የከተማይቱ አስተዳዳሪ ደጃዝማች ወንድወሰን ካሣ ለሚስዮኑ ጉድሙንድሰን በአውሮጳውያን የምግብ አይነት የተዘጋጀ እራት ግብዣ አደረጉ። ጉድመንድሰን የሆስፒታሉን ሥራ ለ፪ ዓመት በኃላፊነት ተቆጣጥሮ ፯ ህንጻወችን አቆመ። ለዚህ ስራ ፹፰ አህዮች፣ ፵፭ በቅሎዎች፣ ፬ ግመሎች እቃ ለማመላለስ ሲጠቅሙ ከአካባቢው ኖራን ( lime) ለማምጣት ፰ ቀን ወስዶ ነበር። በዚህ ወቅት አዲስ አበባ በቴሌግራም ለመገናኘት ፵ ቀናት ይወስድ ነበር፣ መልዕክተኛ ደግሞ ፬ ሳምንት። ኤሪክ ፓልም የተሰኘ ሚስዮናዊ ከህንጻው መጠናቀቅ በኋላ የሚስዮኑ አላፊ ሆኖ አገለገለ። ለዚህ ሆስፒታል መሠራት አነሳሽንተን ወስደው አስተዋጽዖ ያደረጉ ጉድሙንድሰን፣ ዶክተር አንደርሰን፣ ቄስ ስትራህል እና የገንዘብ ኃላፊው ፔደርሰን ነበሩ። [1]

ደብረ ታቦር ሆስፒታል፣ በ፲፱፻፶ ዓ.ም.
  1. ^ G Gudmundsen, Fjorton år .., Sthlm 1936 p 161-169