Jump to content

ደንቀዝ

ከውክፔዲያ
(ከደንካዝ የተዛወረ)
ደንቀዝ
ሱሰንዮስ ቤተመንግስት፣ በደንቀዝ
ደንቀዝ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ደንቀዝ

12°28′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°37′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ደንቀዝ በጣዳ ወረዳ ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ደቡብ ምስራቅ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ የጥንቱ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። አጼ ዘድንግል የመንግስታቸውን ማዕከል ያቋቋሙት እዚህ ቦታ ንበር። አጼ ሱሰንዮስ ቤተ መንግስታቸውን በ1610 ዓ.ም. በዚሁ በደንቀዝ የመሰረቱ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በኒሁ ንጉስ ዘመን መጨረሻ የተገነባ ግምብ እና የካቶሊክ ካቴድራል ፍራሾች በቦታቸው ይገኛሉ። ቤተ መንግስቱ ተሰርቶ ያለቀው በ1622ዓ.ም. ነበር። እንደ የአጼ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል አገላለጽ ደንቀዝ ከተማ ብቻ ሳይሆን የንጉሱ ግዛት መዲና ነበር። በዘመኑ ወደ50፣000 ህዝብ በከተማው ይኖር እንደነበር የፖርቱጋሉ ማኑኤል አልሜዳ በተዘዋዋሪ አሳይቷል። ግምቦቹ የትም አገር ድንቅ ሊባሉ የሚችሉ እንደነበሩ ይሄው አልሜዳ ሳይዘግብ አላለፈም[1]

የደንቀዝ ቤተ መንግስት ከኮረብታ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በስሩ የገዳም ጊዮርጊስ ሸለቆን ያማትራል። በግምቡ ውስጥ ወለል ላይ የተሳሉት ምስሎች አሁን ድረስ ይታያሉ፣ የፈረሱት ክፍሎች መስኮቶች በቅምብብ (አርች) የተሰሩ መሆናቸውን አሁን ድረስ ማየት ይቻላል። የግምቡ ጢስ መውጫ ቺምኔ እና ከግድግዳው ላይ የተሰሩት ዕቃ መደርደሪያወች ተለይተው ይታያሉ። የግምቡ ውጫዊ ክፍል የዝናብ ውሃን ማጠራቀሚያ ልዩ ስልት እንዳለው ማስተዋል ይቻላል። የግምቡ አሸንዳ መሬት ውስጥ ወደተቀበረ ውሃ ማጠራቀሚያ (14ሜትር ርዝመት በ5.5ሜተር ወርድና በ8.5ሜትር ጥልቀት) ያመራል። የግንቡ ቅምብብ ጣሪያም ሳይፈርስ አሁን ድረስ አለ።

የደንቀዝ ካቴድራል በአንጻሩ ስራው የተጀመረው በ1620 ሲሆን በዚህ ወቅት ጀሱይቶች በንጉሱ ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ነበራቸው። የካቴድራሉ ፍራሽ ከቤተመንግስቱ ፍራሽ 300ሜተር በስተ ደቡብ ሲገኝ የአውሮፓ ካቶሊክ ካቴድራሎችን ቅርጽ ይይዛል። 27ሜትር የሚለካው የካቴድራሉ ጣሪያ ድሮ ገና የፈረሰ ነበር። በምዕራብ በኩል ያሉት ደጋፊ ቅምበቦቹ ግን አሁን ድረስ ጸንተው ይታያሉ።

እንደ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል፣ የቤተ መንግስቱ ግምብ የተሰራው በባንያዊው አናጢ አብድል ከሪም እና ግብጻዊው የሰራተኞች አዛዥ ፀደቃ ንስረኒ ነበር[2]። ካቴድራሉን ለማሰራት የጀስዩቱ ጳጳስ አልፎንሶ ሜንዴዝ ሰራተኞችን ከህንድ አገር እንዳስመጣ ይጠቀሳል።

የደንቀዝ ቤተ መንግስት አቅድ
የደንቀዝ ቤተ መንግስት ግድግዳ፣ በአሁኑ ዘመን
የደንቀዝ ካቴድራ አቅድ
የደንቀዝ ካቴድራል በአሁኑ ዘመን


  1. ^ Historia de Etiopía a Alta ou Abassia
  2. ^ የአጼ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል