Jump to content

ደደሆ

ከውክፔዲያ
ደደሆ

ደደሆ (Euclea racemosa) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሁሌ ለም ዛፍ ወይም ቊጥቋጥ አይነት ነው። ብዙ ቅጠላቅጠልና ትንንሽ ቀይ፣ ሐምራዊና ጥቁር ፍሬዎች አሉበት።

አፋርኛና በሶማልኛ የሌላ ዝርያ ዛፍ Salvadora persica «ደደሆ» ይባላል፤ የዚያው ዛፍ ስም በአማርኛ መሮ ነው።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በኮረብቶች ወይም በእዳሪ መሬት ተራ ነው።

በምስራቃዊው አፍሪካ ከግብጽ እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ፣ እንዲሁም በኮሞሮስ፣ በኦማንና በየመን ይገኛል።

የተክሉ ጥቅም

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ትንንሽ ፈሬዎቹ ሊበሉ ይቻላል፤ በትልቅ መጠን ቢበላ ግን የሆድ ማበጥ ያደርጋል። ፍሬዎቹም በአዕዋፍ ይበላሉ።

ፍሬዎቹም «የደደሆ ኮምጣጤ» ለመሥራት ይጠቀማሉ።

ጥቁር ፍሬዎቹ ደግሞ ሐምራዊ ቀለም ለመሥራት ይጠቀማሉ።[1]

ፍቼ በተደረገ ጥናት ዘንድ፣ የደደሆ ቅጠል ዱቄት ለጥፍ ለኪንታሮት ይለጠፋል። የቅጠሉ ጭማቂም ለኮሶ ትል ወይንም ለአባለዘር በሽታ ይጠጣል። አገዳውም ለጥርስ ሕመም ይኘካል።[2]

  1. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች