Jump to content

ዳሚቅ-ኢሊሹ

ከውክፔዲያ

ዳሚቅ-ኢሊሹ ከ1731 እስከ 1709 ዓክልበ. የኢሲን ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንጉሥ ነበረ። በዚያው አመት የባቢሎን ንጉሥ ሲን-ሙባሊት ከብዙ ጦርነት በኋላ ከተማውን ያዘ።

ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ መጨረሻው ስም ነው። ዝርዝሩም በእርሱ ዘመን የተቀናበረው ይመስላል። በዚያ ዘንድ ዘመኑ 23 ዓመታት ነበር። በላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲን 9ኛው እስከ 21ኛው አመት (በ1726-1714 ዓክልበ.) ዳሚቅ-ኢሊሹ ኒፑርን ከላርሳ እንደ ያዘ ይመስላል።

ቀዳሚው
ሲን-ማጊር
ኢሲን ንጉሥ
1731-1709 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
የለም (ሲን-ሙባሊት ኢሲንን ያዘ)