Jump to content

ዴርቶጋዳ

ከውክፔዲያ

ዴርቶጋዳ በ ፪፼፩ዓ.ም.በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ የቀረበ ልብ-ወለድ ሲሆን ሳይንሳዊ ዘዉግ ያለዉ የኢትዮጵያን አንድነት የሚስብክ መጽሀፍ ነዉ። መፅሀፉ በአንድ አመት ብቻ አስር ጊዜ በመታተምና በመጀመሪያ እትሙ ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ኮፒ በመሸጥ በሀገራችን የመፅሀፍ ሽያጭ ደረጃ የመጀመሪያው ነው።

መጽሀፉ ለዶ/ር ኢ/ር ቅጣዉ እጅጉ ማስታወሻነት ተበርክቷል።ከብዙ በጥቂቱ ገፀ-ባህሪያቱ ሻጊዝ እጅጉ(በእዉኑ አለም ቅጣዉ እጅጉ )፣ሚራዥ፣ሲጳራ፣ሜሮዳ፣ዣንጊዳ፣ጌራ፣አባ ፊንህሰ፣አባ ዠንበሩ ..።ዴርቶጋዳን የኢትዮጵያን ስነ-ጽሁፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደ ብለዉ ብዙ የኢትዮጵያ ሙህራን ጽፈዋል.ይስማዕከ የዴርቶጋዳን ቀጣይ ክፍል ዴርቶጋዳ ፪(ራማቶሃራን)ለህትመት ዴርቶጋዳን በጻፈ በአመቱ ፪፼፪ አብቅቷል። ይህ ያለዉን ችሎታ ያሳየናል።አንዳንድ ጥራዝ ንጠቅ ሀያሲያን ይስማዕከን ሲተቹ ይስማዕከ የሰጠዉ መልስ "ትችቶች ምንም መጥፎ ቢሆኑ ይበልጥ እንድሰራ ያደርጉኛል"።ቢሆንም ቅሉ ይስማዕከ በስራዎቹ በኢትዮጵያዊያን ልብ ዉስጥ ለዘላለም ይኖራል።ይስማዕከ በመጽሀፉ ብዙ ነገሮችን ለመጥቀስ ሞክሯል ስለ መልካም አስተዳደር እጦት በኢትዮጵያ፣ስለ ጥንት ኢትዮጵያዊያን ጀግንነትና ተጋድሎ፣ስለ ፍቅር፤ስለ ኢትዮጵያዊያን ሙህሮች... በአሁኑ ሰዓት ይስማዕከ ዴርቶጋዳ እስከ "ዮቶድ" ድረስ ለህትመት አብቅቷል። እነሱም፥ ዴርቶጋዳ፣ ራማቶሃራ፣ ዣንቶዣራ፣ ዮራቶራድ እና ዮቶድ ናቸው። ይስማዕከ ወርቁ በአጠቃላይ ሁለት የግጥም መድብሎች እና አሰራ ሶስት ረጂም ልቦለዶችን ለንባብ ያበቃ የዘመናችን እንቁ እና ተወዳጅ ደራሲ ነው።