ዶሮ ኮተሌት
Appearance
- 4 የጸዳ የዶሮ መላላጫ (600 ግራም ያህል የሚመዝን)
- 2 የቡና ስኒ (100 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
- 2 የተመታ እንቁላል
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 4 የቡና ስኒ (200 ግራም) የዳቦ ዱቄት
- ሥጋውን በሥጋ መቀጥቀጫ መጠፍጠፍ፤
- ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና የፉርኖ ዱቄቱን መቀላቀል፤
- ሥጋውን በተቀላቀለው ዱቄት መለወስ፤
- የተመታው እንቁላል ውስጥ እየነከሩ ካወጡ በኋላ የዳቦ ዱቄቱ ላይ መተምተም፤
- ሥጋውን አራት ማዕዘን ቅርጽ መስጠት፤
- የጋለ ዘይት ውስጥ ቅርጽ በተሰጠው በኩል መጥበስ፡፡