ሰኸምሬ ጀሁቲ
Appearance
(ከጀሁቲ የተዛወረ)
==
ሰኸምሬ ሰመንታዊ ጀሁቲ | |
---|---|
ጀሁቲ ያለበት ድንጋይ | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1646-1643 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰኸቀንሬ ? |
ተከታይ | 8 ሶበክሆተፕ |
ሥርወ-መንግሥት | 16ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ሰኸምሬ ሰመንታዊ ጀሁቲ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1646-1643 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ስሙ «ሰኸምሬ ሰመንታዊ ጀሁቲ» የሚታወቀው ከአንዳንድ ቅርስ ብቻ ነው።
- 1) የታችኛ ግብጽ ዘውድ ለብሶ የሚያሳይ ድንጋይ ክፍል አለ። ከዚህና ከስሙ «-ታዊ» በታችኛ ግብጽ ላይ ይግባኝ እንደ ጣለ ሊገመት ይችላል። ሆኖም ይህ በሂክሶስ ዘመን ስለ ነበር፣ እንዲሁም አቢዶስ በአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ስለሚታሰብ፣ ጀሁቲ በእውነት በታችኛ ግብጽ ላይ እንደ ገዛ አይታሰብም።
- 2) አንድ ሌላ ስሙ የተቀረጸበት ድንጋይ
- 3) የሚስቱ ንግሥት መንቱሆተፕ ኮስሞቲክ ሳጥን በመቃበርዋ ሲገኝ ስሙ ተገኘበት።
- 4) በካርናክ ፈርዖኖች ዝርዝር ላይ «ሰኸምሬ ሰመንታዊ» የሚባል ፈርዖን ይዘረዘራል። ይህ ሰነድ ግን ምንም ቅድም-ተከተል አይጠብቅም።
- 5) በቶሪኖ ቀኖና ላይ በአንድ ክፍል «ሰኸምሬ ፫ አመት፣ ሰኸምሬ ፲፮ አመት፣ ሰኸምሬ... ፩ አመት» ሲል ይህ ክፍል ባብዛኛው የ16ኛው ሥርወ መንግሥት እንደ ሆነ ይታመናል። መጀመርያው የተዘረዘረው ሰኸምሬ ጀሁቲ እንደ ነበር ይገመታል።
ቀዳሚው ሰኸቀንሬ ? |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1646-1643 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 8 ሶበክሆተፕ |