ጀጎል ግንብ
Appearance
የጀጎል ግንብ በ1551-1552 በንጉስ/አሚር ኑር ቢን ሙጃሂድ እንደተገነባ የታሪክ መዛግብት ያመላክታሉ። ይህ ግንብ ከምድር ከ4-5 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ወርዱ ደግሞ ከ50-75 ሴንቲሜትር ይሰፋል። አጠቃላይ ስፋቱ 48 ሄክታር ነው። የግምቡ መፈጠር ዐቢይ ምክንያትም የሐረር ሕዝብን ከጠላት ጦረኞች ለመታደግ ተብሎ እንደ ተሰራ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ግንቡ አምስት በሮች ያሉት ሲሆን ውሃ ያለበትን አቅጣጫም ለማመልከት የተሰሩ ናቸው። የጀጎል አምስቱ ጥንታዊ ዋና ዋና በሮች:-
በሐረሪ
1, አስማጂን በሪ
2, በድሪ በሪ
3, ሱጉድአጥ በሪ
4, አርጎባ በሪ
5, አሱሚይ በሪ
በአማርኛ
1, ሸዋ በር
2, ቡዳ በር
3, ሰንጋ በር
4, ኤረር በር
5, ፈላና በር
በሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራው ዱክ በር ወይም መስፍን በር : አሁን ብዙዎቹ የሚጠሩት ሐረር በር ከጥንታዊዎቹ ጋር የማይገናኝ ነው። ብዙ ሰዎች የጥንቱን አምስት በሮች ጥሩ ሲባሉ፣ የሐረር በርንም ያካትታሉ። ባይሆን ስድስተኛው ብለን፣ በቅርቡ የተሰራ ብለን ልንጠራው እንችላለን።