ጅማ ዩኒቨርስቲ

ከውክፔዲያ

ጅማ ዩኒቨርስቲኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ነው። ይህ ተቋም የሚገኘው በኦሮሚያ ክልልጅማ ዞን (ጅማ) ውስጥ ነው። ተማሪዎችን በተለያዩ ዘርፎች በዲግሪ እና በተለያዩ ደረጃዎች ያሠለጥናል። በቀድሞው ስሙ ጅማ የግብርና ኮሌጅ እና የጅማ የጤና ሳይንስ ተቋም በጋራ የነበረ ሲሆን ከታኅሣሥ 1992 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊያድግ ችሏል። ዋናው ካምፓስ የሚገኘው ከቀድሞው የጅማ ንጉስ አባ ጅፋር ቤተ መንግስት ቀጥሎ ነው።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፋኩልቲዎች እና የትምህርት ክፍሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 63/1999 እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 22 ቀን 1999 ዓም በወቅቱ የግብርና ኮሌጅና የጤና ሳይንስ ኢንስቲተዩት ተብለው የሚጠሩ ሁለት ተቋማት በመዋሃድ የተቋቋመ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው፡፡ ዛሬ በአገሪቱ ካሉ አንጋፋና በተለይ በማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ፍልስፍናው ፈር-ቀዳጅና መሪ የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲ “We Are in The Community በሚለው መርህ የታወቀ ተቋም ሲሆን ከምስረታው ጀምሮ በስልጠና፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በርካታ ድሎችን ያስመዘገበና በትምህርት አሰጣጥ ጥረቱ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ አንደኛ የወጣ ብቸኛ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ በምስረታው ወቅት በጥቂት የጤና፣ ህክምናና ግብርና መስኮች በአብዛኛው ዲፕሎማ መርሃ-ግብሮችን በማስተማር ላይ ተወስኖ የነበረ ሲሆን ይህ ሁኔታ ዛሬ በአስገራሚና ፈጣን ለውጥ ተቀይሮ በዚህ ዓመት በ62 የቅድመ-ምረቃ፣ በ139 ሁለተኛ ዲግሪና በ35 ሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች 40587 ተማሪዎች ተቀብሎ ያስተምራል፡፡ አምስት ካምፓሶች ያሉት ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ 7864 ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ መካከል 6016 የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችና 1848 ኢትዮጵያዊ መምህራኖችን የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው፡፡

ዋናው ካምፓስ ውስጥ የዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራር፤ ማዕከል ቢሮዎች፣ ሦስት ኮሌጆችና የተቋሙ መማሪያ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ከዋናው ግቢ በ4 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ስምንት ትምህርት ክፍሎች ያሉት ካምፓስ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኪቶ ፉርዲሳ ካምፓስም ከዋናዉ ግቢ በ6 ኪሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከዋናው ግቢ አጥርና መንገድ ባሻገር በስተደቡብ የሚገኘው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ካምፓስ 4 የትምህርት ክፍሎች ይዟል፡፡ ከጅማ ከተማ 42 ኪሜ ርቆ የሚገኘው የአጋሮ ካምፓስ በግንባታ ላይ ሲሆን ይህም አምስተኛው ካምፓስ ነው፡፡

በአገሪቱ እጅግ ልዩ በሆኑ የትምህርት ፕሮግራሞች በተለይም በባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግና ጥርስ ህክምና ትምህርት ዘርፎች ፈር ቀዳጅ የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ትምህርት ባህልን በመገንባትና መሰረታዊ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ምርምሮች በማካሄድ ዓለማቀፋዊነትን በማስፋፋትና መላሽ ሰጪ አገልግሎቶች በመስጠት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ አገራችንን ከድህነት አረንቋ ለመታደግና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍ በሠው ኃይል አቅም ግንባታ ዘርፍ አያሌ ሚና በመጫወት ላይ ያለው ጅማ ዩኒቨርሲቲ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተመርኩዞ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና ስትራቴጂካዊ ስልቶችን ማስተግበር የሚያስችል ዓመታዊ ዕቅድ በማውጣት በርካታ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን ዋነኛ ተልዕኮ የሆኑትን መማር/ማስተማር፤ ምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት ተልዕኮዎች ለማሳካት ጥረት እየተደረገ ነው፡ ፡በተመሳሳይ ማህበረሰባችን የራሱን ችግሮች በራሱ እንዲፈታ ለማስቻል፣ የኢንቬስትመንት አቅማችንን ለመገንባትና ከባለድርሻዎቻችን ጋር እኩል ተጠቃሚ የሚያደርጉ ትስስሮችን በመፍጠር ራዕይ ዕውን ለማድረግ ርብርብ እየያደረገ ሲሆን በዚህም አዳዲስ ዕውቀትና ክህሎት ማንጨት የሚያስችሉ አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፤ ለአገሪቱ አንገብጋቢ ችግሮች አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት በሚያስችሉ የትኩረት መስኮች ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

ካምፓሶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]