Jump to content

ጅዮንግ

ከውክፔዲያ

ጅዮንግ (ቻይንኛ፦ 扃) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገበው እንዲህ ነው፦ በ1687 ዓክልበ. ግድም ትልቅ ወንድሙ ቡ ጅያንግ ዘውዱን በፈቃድ ትቶ ጅዮንግ ተከተለው። በ፲ኛው ዓመት (1678 ዓክልበ. ግ.) በ ጅያንግ ዓረፈ። በ፲፰ኛው ዓመት 1669 ዓክልበ.ግ. ጅዮንግ ዓረፈና ልጁ ጂን ተከተለው።

ቀዳሚው
ቡ ጅያንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1687-1669 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ጂን