ጂን

ከውክፔዲያ

ጂን (ቻይንኛ፦ 廑) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር። ሌላ ስሙ ዪንጅያ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገበው እንዲህ ነው፦ በመጀመርያው ዓመት በሆ ወንዝ ምዕራብ ኖረ። በ፬ኛው ዓመት «የምዕራብ ሙዚቃ» ቃነ፤ የኩንዉወይ ገዥ ጂ ታን ወደ ሹዦው ተዛወረ። በ፰ኛው ዓመት (1661 ዓክልበ.) በታምራዊ ትርዒት አሥር ፀሐዮች አብረው በሰማይ ታዩ፤ በዚያም አመት ጂን ዓረፈና የአጐቱ ቡ ጅያንግ ልጅ ኮንግ ጅያ ተከተለው።

ቀዳሚው
ጅዮንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1669-1661 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኮንግ ጅያ