ግዕዝ ኣልቦ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ግዕዝ ኣልቦ ፊደል በላቲኑ ወይም ኣረቡ ኣልቦ ኣኃዝ ("0") ምትክ እንዲያግለግል የተሠራ ኣዲስ የኣኃዝ ምልክት ነው። የግዕዝ ፊደል ከጥንት ፊደላት ኣንዱ ስለሆነ የኣልቦ ቍጥር ምልክት ከሌላቸው ፊደላት ኣንዱ ነበር። ፊደሉን ለሟሟላት ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶ/ር ኣበራ ሞላ የግዕዝን ኣልቦ ፈጥረው ከ፴ ዓመታት በላይ ጥቅም ላይ ውለዋል።

ኣልቦው ጥቅም ላይ እንዲውል ዶክተሩ ከ"1" እስከ "9" ተጨማሪም ኣኃዞች በመጨመር የግዕዝን ቍጥሮች ብዛት ከ፳ ወደ ፴ ከፍ ኣድርገዋቸዋል።