Jump to content

0

ከውክፔዲያ
0
non-positive integerintegereven numbernon-negative integerautomorphic numberFibonacci numberadditive identityMotzkin number
part ofsingleton of 0 አርም
described at URLhttps://turkic.elegantlexicon.com/turkforms.php?form=zerozero አርም
hashtagzero አርም
notation0 አርም
maintained by WikiProjectWikiProject Mathematics አርም
mathematical inverse0no value አርም
code0-----0𐆊 አርም
opposite of0አዕላፍ አርም

0 ወይንም ዜሮ ወይንም ቁጥር ጽሕፈት ወቅት የባዶነት ማመላከቻ ምልክት ነው። ዜሮ በራሱም ቁጥር ሲሆንም ያንድን መለኪያ ባዶነት ያመለክታል። ለምሳሌ የባዶ ስብስብ አባላት ቁጥር ዜሮ ነው እንላለን።

የዜሮ ፅንሰ ሐሳብ በባቢሎኒያኖች የፈለቀ ሲሆን ይኼውም በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ነበር። ሆኖም ባቢሎኒያኖቹ ዜሮን እኛ እንደምንጠቀምበት ሳይሆን እንደ ቦታ ያዢ ምልክት ነበር የጠቀሙበት። ለምሳሌ 304፣ ወይንም 450 ሲጽፉ፣ 0 እዚህ ላይ የቁጥር አለመኖርንና ቦታ መያዝን ብቻ ያመላክታል።

ዜሮን እኛ በምንጠቀምበት መልኩ የተጠቀሙት ህንዶች ሲሆኑ ይሄውም ቢያንስ ከ620 ዓ.ም. ጀምሮ ነበረ።[1] ለህንዶች፣ ዜሮ ቦታ መያዣ ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ እራሱን የቻለ ቁጥር ሲሆን ለስሌት የሚረዳ ነበር። በህንዶች ዘንድ 0 ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ለማካፈልና ለማባዛት ግልጋሎት ይውል ነበር።

768 ዓም ጀምሮ አረቦች ከህንዶች የዚህን ቁጥር ጥበብ በመቅሰም ለአዲሱ ቁጥር ስፍር صفر የሚል ስያሜ ሰጡት። ትርጓሜውም ባዶ ማለት ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ (0) ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ።

ከዚያ ቁጥሩ መጀመርያ በአውሮፓዊ መጽሐፍ የተጠቀሰው በ968 ዓም ነበር። ከአረቦቹ ይህን ቁጥር የቀሰመው ጣሊያኑ ፊቦናቺ «ስፍር» የሚለውን ወደ ዜፊሮ በመቀየር የቁጥሩ ጥቅም በተለይ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. አውሮጳ እንዲስፋፋ ሆነ። በኋላም በእንግሊዝኛ «ዜፊሮ» ወደ «ዜሮ» ተለውጦ ስሙ በዚህ ረጋ።

የዜሮ ጠባዮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • መደመር: x + 0 = 0 + x = x. ዜሮን ሌላ ቁጥር ላይ መደመር ያን ቁጥር አይለውጥም
  • መቀነስ: x − 0 = x and 0 − x = −x.
  • ማባዛት: x · 0 = 0 · x = 0.
  • ማካፈል: 0|x = 0, x እዚህ ላይ ዜሮ ያልሆነ ቁጥር ነው። በአንጻሩ x|0 ያልተተርጎመ ነው።
  • ንሴት: x0 = x/x = 1, ይህ የማይሰራው x = 0 ሲሆን ብቻ ነው። በተጨማሪ ለማንኛው እውን ቁጥር x, 0x = 0.
  1. 2010 ዓም፣ ተመርማሪዎች በ«ካርቦን ዝመና» ዘዴ በኩል ዜሮ የሚጠቀምበት አንድ ሰነድ ከ200-400 ዓ.ም. እንደ ሆነ አሳወቁ። «ካርቦን ዝመና» ግን እጅግ አጠያያቂ ዘዴ ነው።