ጎርፍ

ከውክፔዲያ
በዝናብ እና ትልቅ ማዕበል የተከሰተ ጎርፍ በዳርዊንሰሜናዊ ግዛትአውስትራልያ
ንጉሥ አብዱላ ጎዳና ተጥለቅልቆ በጅዳሳዑዲ አረቢያ
በኸሪኬን ዊልማ በኦክቶበር 2005 እ.ኤ.አ. የተከሰተ ጎርፍ ኪይ ዌስትፍሎሪዳአሜሪካ አካባቢ
ጎርፍ በናታል፣ ሪዮ ግራንድ ዶ ኖርቴብራዚል ውስጥ (ኤፕሪል 2013 እ.ኤ.አ.
በከባድ ዝናብ የተከሰተ ፈጣን ጎርፍ በቱዉምባክዊንስላንድአውስትራልያ

ጎርፍ ወይም የውሃ መጥለቅለቅ ማለት በተለምዶ ደረቅ የሆነ መሬት በውሃ መሞላት ነው። ጎርፍ ብዙ ጊዜ በመኖሪያና የንግድ ተቋማት ላይ ጉዳት ያደርሳል። ሆኖም በወንዞች አካባቢ ያለው መሬት ጠፍጣፋ እና ለም ስለሆነ ሰዎች በውሃ ዳርቻ ይሠፍራሉ። አንዳንድ ጉርፎች ቀስ ብለው የሚያጥለቀልቁ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ በጥቂት ደቂቃዎች በፍጥነት ይሞላሉ።

ዋና የጎርፍ ዓይነቶች እና መንስዔዎቻቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከዝናብ ጋር የተያያዘ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በጠፍጣፋ ወይም ዝቅ ባለ ቦታ ላይ የዝናብ ውሃ ወደ መሬት ቶሎ መዝለቅ ካልቻለ ወይም በአስፋልት ወይም ሌላ ደረቅ ንጣፍ ከተከለከለ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል።

የወንዝ ሙላት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተከታታይ ዝናብ ወይም ፈጣን የበረዶ መቅለጥ ወንዝ እንዲሞላና እንዲያጥለቀልቅ ያደርጋል። ይህም ክስተት በመሬት መንሸራተት፣ ቆሻሻ ወይም ሌላ እንቅፋት ሊባባስ ይችላል።

የባህር ዳርቻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በባህር ዳርቻ እና በወንዝና ባህር መገናኛ /estuary/ ቦታ ላይ በነፋስ እና ዝቅ ያለ የአየር ግፊት የሚከሰት የውሃ ማዕበል ጎርፍን ሊያስከትል ይችላል። በአውሎ ነፋስ ወይም ሱናሚ /tsunami/ የሚነሳ መጥለቅለቅም በዚህ ክፍል ውስጥ ይመደባል።

ድንገተኛ አደጋ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እንደ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም እሳተ ገሞራ ያሉ ድንገተኛ አደጋዎች ጉርፍ ሊያስነሱ ይችላሉ። በተጨማሪም በግድብ መፍረስ ወይም ሌላ የመሰረተ ልማት መበላሸት የሚከሰት ጎርፍ በዚህ ምድብ ውስጥ ይጠቃለላል።

ጉዳት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ወዲያው የሚከሰት ጉዳት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጎርፍ ዋና ጉዳቶች የሰውና እንስሳ ሞት፣ የሕንጻዎች መፍረስ እና የመንገድ፣ ድልድይና ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ መበላሸት ናቸው።

የመሠረተ ልማት መውደም የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ እና ማመንጫዎችን ከሥራ ውጭ ሊያደርግ ይችላል። የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ደግሞ በርካታ ሂደቶችን ያስተጓጉላል። ለምሳሌ የውሃ ማጣሪያ እና ማቅረቢያ ተቋማት አገልግሎት ሊያቆሙ ይችላሉ።

የንፁህ ውሃ እጥረትና የፍሳሽ ውሃ ከጎርፍ ጋር መቀላቀል እንደ ታይፎይድ እና ኮሌራ ዓይነት የውሃ ወለድ በሽታዎች መንስዔ ሊሆን ይችላል።

በመንገድ እና ሌላው መሠረተ ልማት ላይ የደረሰ ጉዳት የጎርፍ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ለመርዳት ወይም በአስቸኳይ ለማከም በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ይሆናል።

በጎርፍ የተጥለቀለቀ የእርሻ መሬት ላይ እህል መዝራት ወይም መሰብሰብ ስለማይቻል ከጥቅም ውጪ ይሆናል። ይሄም ለምግብ እጥረት ይዳርጋል። ጎርፉ እጅግ በጣም ከፍተኛ ከሆነ የአንድ አገር እህል በሙሉ ሊጠፋ ይችላል። አንዳንድ የዛፍ ዝርያዎች ለረዥም ጊዜ ስራቸው በውሃ ከተጥለቀለቀ በሕይወት ላይቆዩ ይችላሉ።[1]

የረጅም ጊዜ ጉዳት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቱሪዝም መዳከም፣ የመጠገኛ ወጪ እና የቁሳ ቁስ ዋጋ ንረት በኢኮኖሚው ላይ የሚያደርገው ተጽዕኖ በአብዛኛው ጊዜ ከከፍተኛ መጥለቅለቅ በኋላ ይታያል። የሰው ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም የሥነ ልቦና ችግር ሊፈጥር ይችላል።

የጎርፍ ትንበያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጉርፍ ከመድረሱ በፊት መተንበይ ቅድመ ጥንቃቄዎች እንዲወሰዱ እና የሚመለከተው ህብረተሰብ እንዲጠነቀቅ ጊዜ ያሰጣል።

ትክክለኛ ትንበያ ለመስጠት የአንድ ወንዝን ፍሰት ከዝናብ መጠን ጋር የሚያገናኝ ታሪካዊ መረጃ ወይም ሬከርድ ያስፈልጋል። ይህን ታሪካዊ መረጃ ከጊዜው የአየር ትንበያ እና የአካባቢው መሬት ሁኔታ ጋር በመቀላቀል የጎርፉን መድረሻ ጊዜ እና ከፍታ አስቀድሞ መገመት ይቻላል።

ማመዛገቢያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Stephen Bratkovich, Lisa Burban, et al., "Flooding and its Effects on Trees", USDA Forest Service, Northeastern Area State and Private Forestry, St. Paul, MN, September 1993, webpage: Na.fs.fed.us-flood-cover Archived ጁን 14, 2016 at the Wayback Machine. (እንግሊዝኛ)

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]