Jump to content

ጎንደሻፑር አካዳሚ

ከውክፔዲያ

ጎንደሻፑር አካዳሚጎንደሻፑርፋርስ የነበረ የኔስቶራዊ ክርስትና ከፍተኛ ትምህርት ቤት ነበረ። ያቀረባቸው ትምህርቶች በሕክምናፍልስፍናስነ መለኮትስነ ፍጥረት ነበሩ።

መጀመርያ እንደ ኔስቶራዊ ገዳም በ263 ዓም ተመሠረተ። ከ521 ዓም ከፋርስ መንግሥት ንጉስ ኾስራው ጀምሮ ዝነኛ ትምህርት ተቋም ሆነ። ከቢዛንታይን የሸሹት ኔስቶራዊ ስደተኞች የሕክምና፣ ስነ ፈለክ፣ እና የፍልስፍና መጻሕፍት ከአረማይስጥ ወይም ከግሪክኛ ወደ መካከለኛ ፋርስኛ እንዲያስተርጒሙ አደረገ። እንዲሁም መምህሮች ከሕንድ ጠርቶ የስነ ፈለክ፣ ሥነ ቁጥርና የሕክምና መጻሕፍት ከሳንስክሪት ወደ መካከለኛ ፋርስኛ እንዲያስተርጓሙ አደረጋቸው። እንዲሁም መምህሮች ከቻይና ጠርቶ የባህላዊ ሕክምናና የሃይማኖት መጻሕፍት ከቻይንኛ አስተረጎሙ።

የሕክምና ተቋም ሀኪሞች ግን በአራማይስጥ ይጽፉ ነበር፤ አረማይስጥ በሕክምና ዘርፍ እንደ መደበኛ ቋንቋ ተመሠርቶ ነበርና።

ይህ ተቋም በሕክምናና በስነ ቁጥር አደረጃጀት ወሳኝ ሚና አጫወተ።