Jump to content

ጤና ኣዳም

ከውክፔዲያ
(ከጤና አዳም የተዛወረ)
ጤና አዳም

ጤና ኣዳም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። ጤር አደም

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

Ruta chalepensis ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያድገውና የታወቀው ጤና ኣዳም ነው። ዶ/ር ፈቃዱ እንደጻፉት ሌላ ዓይነትም ኣለ። ከፈረንጅ ጤና ኣዳም (Ruta graveolens) ጋር እንዳይምታታ መለየት ከሚቻልባቸው ኣንዱ በኣበባዎቹ ነው።

== በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር=ወይናደጋማ ቦታ

የተክሉ ጥቅም

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባህላዊ መድሃኒት፣ የጤና አዳም ቅጠል ጭማቂ በቡና ኢንፍሉዌንዛን ለማከም እንደሚረዳ ተዘግቧል።[1]‎ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ ተክሉ እንደ ‎‎ትኩሳት‎‎ እና ‎‎እብጠት‎‎ላሉ በርካታ ህመሞች እንደ ‎‎ዕፅዋት መድኃኒት‎‎ነት ያገለግላል .‎ እንዲሁም የጤና አዳም ቅጠልና ፍሬ ማኘክ ለመጋኛ ወይም ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ያገለግላል። ቅጠሉና ፍሬው ከፌጦ ዘር ጋር ሲበላ ለሆድ ቁርጠት መፍትሄ ይሆናል። ከፌጦ ዘርና ከጠጅ ሳር ሥር ጋር ተቀላቅሎ ደግሞ ለሆድ ቁርጠት፣ ወይም ለከብት ጎሎባ ይሠጣል። በተጨማሪም የጤና አዳም ቅጠልና ፍሬ ከጠጅ ሳር ሥር፣ ከነጭ ሽንኩርትና ከኣጣጥ ቅጠል ጋር ተቀላቅሎ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።[2] ወይም ቅጠሉ ከነጭ ሽንኩርትና ውሃ ጋር ተቀላቅሎ ብቻ ለሆድ ቁርጠት ይጠጣል።[3]

ጤና አዳም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እና በአውሮፓ ሲገኝ የተለያዩ ዝርያዎችም አሉት ከነዚህም መካከል በ አውሮፓ እና በሰሜን አፍሪካ ፣ ምስራቅ አፍሪካ ኢትዮፕጲያ የሚገኙት ተጠቃሽና ዋነኞቹ ናቸው። ጤና አዳም በ አበባ የሚራባ የዕጽዋት ዝርያም ጭምር ነው።

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  3. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች