ከውክፔዲያ

(ቻይንኛ፦ 發) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር። የቀዳሚው የጋው ልጅ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገበው እንዲህ ነው፦ በመጀመርያው ዓመት የተለያዩ ያልሠለጠኑ አሕዛብ ወደ ግቢው በር ለማክበር ተሰበሰቡ። በላይኛ ኩሬ ቦታ ጭፍራዎችን አሳዩ። በ፯ኛው አመት የመሬት መንቀጥቀጥደብረ ታይሻንዶንግ ሆነና ንጉሥ ፋ ዐረፉ። ልጁ ተከተለው።

ቀዳሚው
ጋው
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1649-1642 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ