Jump to content

ፒዩሽቲ

ከውክፔዲያ

ፒዩሽቲ በ1662 ዓክልበ. ያህል የሐቲ (ሐቱሳሽ) ንጉሥ ነበር።

ካነሽ ንጉሥ አኒታ ዐዋጅ ስሙ ይጠቀሳል፤ እንዲህ ሲል፦

«ዳግመኛ የሐቲ ንጉሥ ፒዩሽቲ መጣ። በሻላምፓ ከተማ ያመጣቸውን ትርፍ ሥራዊቱን አሸነፍኩ። ... ሐቱሳሽ በኔ ላይ በክፋት ተባብሮ ስላልሆነ፣ ተውኩት። በኋላ ግን ረሃብ በደረሰበት ጊዘ ጣኦቷ ከተማውን ሰጠችኝ። በሌሊት በኃይል ወሰድኩት። በሥፍራው ፌጦ ዘራሁ። ከኔ በኋላ የሚነግሥ ሁሉ፣ ሀቱሳሽን ዳግመኛ የሚሠፍረው ማናቸውም ሁሉ፣ ጣኦቱ ይመታው! »

ሆኖም ከመቶ ያህል አመታት በኋላ የኩሻራ ሰው 1 ሐቱሺሊ እንደገና ሠፈረው፤ ሐቱሻም ዳግመኛ ዋና ከተማ ሆነ። ይህም የኬጥያውያን መንግሥት መሠረት ነበረ።