ባላ
Appearance
(ከፓራቦላ የተዛወረ)
- ይህ መጣጥፍ ስለ ሥነ ሂሳባዊው መስመር ነው። ለሰዶም ንጉሥ፣ ባላ (የሰዶም ንጉሥ) ይዩ።
ባላ (ፓራቦላ) በሂሳብ ጥናት ውስጥ የተስተካከለ የባላ ቅርጽ ያለው የሂሳብ መስመር ነው ቃል ነው። ባላ በሂሳብ እንዲህ ሲደረግ የፈጠራል፡ ባንድ ጠፍጣፋ ሜዳ ላይ አንድ ነጥብና አንድ መስመር እንውሰደ። ለዚህ ነጥብ እና ለመስመሩ እኩል ርቀት ላይ የሆኑ ነጥቦቹን በሜዳው ላይ ብንደረድር የምናገኘው ስዕል ባላ/ፓራቦላ ይሆናል ማለት ነው። ነጥቡ ፎከስ ሲባል፣ መስመሩ ዳይሬክትሪክስ ይባላል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ኳድራቲክ እኩልዮሽን ይመልከቱ
y = −p ዳይሬክትሪክስ መስመር ቢኖን እና ፎከሱ (p, 0) ቢሆን (x, y) ደግሞ የባላው ነጥቦች ቢሆኑ፣ ከነጥቡና ከመስመሩ ያሉትን እኩል ርቀቶች ግምት ውስጥ በማስገባት ይህን እናገኛለን
ሁለቱንም ጎኖች በየራሳቸው ስናበዛና ስናስተካክል ይህን እናገኛለን
ይህን ባላ በሜዳው ሁሉ ስናዘዋውረው ይህን መልክ ይይዛል
እንግዲህ ይህ ሲስተካከል
የሰጣል። በሂሳብ ጥናአት የባላ አጠቃላይ ቀመር ተብሎ የሚታወቀው ነው
- የተተኮሰ ጥይት፣ የተወረወረ ድንጋይ፣ ሮኬቶች፣ ወዘተ.... በምድር ግስበት ምክንያት እንዲሁ የባላ ቅርጽ ይዘው ለመጓዝ ይገደዳሉ።