ፓርቴኖን በአቴና ከተማ፣ ግሪክ አገር በ446 ዓክልበ. የተጨረሰ ዝነኛ ሥነ ሕንጻ ነው። ለ900 ዓመታት ያህል እስከ 427 ዓም ድረስ የአቴና (ጣኦት) አረመኔ ቤተ መቅደስ ነበረ። ሕንጻው ከ600 ዓም በፊት ቤተ ክርስቲያን ሆነ፣ ከ1500 ዓም በፊት ደግሞ የኦቶማን ቱርክ መስጊድ ሆነ። በ1679 ዓም ህንጻው በጦርነት ፍንዳታ ተጎዳ፣ ፍርስራሹ እስካሁንም ድረስ በአቴና ከተማ ሊታይ ይችላል።