ፕሪቶሪያ
Appearance
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 1,541,300 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,249,700 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 25°45′ ደቡብ ኬክሮስ እና 28°12′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ፕሪቶሪያ በ1847 ዓ.ም. በቦር (አፍሪካንስ) ሕዝብ ተሠራ። በ1852 የደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ሆነ።
ፕሪቶሪያ የአገሩ 'አስተድዳሪ ዋና ከተማ' ሲሆን ቤተ መንግሥት የሚገኘው ግን በኬፕታውን፣ ላይኛ ችሎቱም በብሉምፎንተን ነው።
የአሁኑ መንግሥት ስሙን ወደ ቿኔ ለመቀየር ይፈልጋል። ነገር ግን ይህ አሣብ ብዙ ክርክር አገንቷል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |